Friday, November 20, 2015

የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን


To listen to Deutche Welle Click HERE
Germany (DW) — የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን በተመለከተ፤ የፌድራል መንግስትም ሆነ የኦሮሚያ ምክር ቤት፤ ሕዝብን ጠርቶ ያላወያየበት ምክንያት፤ የኦሮሞ ወይም የአከባቢ አርሶ አደሮችን አፈናቅለዉ መሬት ዘረፋ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ለማድርግ በመታቀዱ ነዉ ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ።
በሌላ በኩል ማስተር ፕላኑ ለአከባቢዉ ነዋሪዎች ስለሚያመጣዉ ጥቅምና ጉዳት በቂ ማብራርያ አይሰጥም የሚሉ እንዳሉም ተመልክቶአል። በአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በመባል የሚታወቀዉን በተመለከተ የፌድራል መንግስትንም ሆነ የኦሮምያ ምክር ቤት ሕዝብን ጠርቶ ያላወያየበት ምክንያት የኦሮሞ ወይም የአከባቢ አርሶ አደሮችን አፈናቅሎ መሪት ዘረፋ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ለማድርግ የታቀደ በመሆኑ ነዉ ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ከፍተኛ አመራሮች ተቹት።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ካሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ የሆነዉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጃ የጋራ ማስተር ፕላን ላይ ለመወያየት ባለፈዉ እሁድ በቡራዩ ከተማ ላይ የጠራዉ ህዝባዊ ስብሰባ መሰረዙ ይታወቃል። ማስተር ፕላኑን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉትን የኦሮሚያ ክልሎችን ከአዲስ አበባ ጋር ለማቀላቀል የኦሮሚያ ምክር ቤት አወጅ እንዳፀደቀና ኮንግሬሱም እሄን በተመለከተ በቡራዩ፣ በላጋ ጣፎ፣ በገላን፣ በሱሉልታና የመሳሰሉ ከተሞች ላይ ከሕዝብ ጋር ለመመካከር አቅዶ እንደነበር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ቃል አቀባይ አቶ በቀለ ናጋ ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።ይሁን እንጂ እሄን ምክክር በቡራዩ ከተማ ላይ ለማድረግ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 28 ቢታቀድም ለብአዴን ስብሰባ ስቴዲዮምም ሆነ አደራሽ እንደታያዘ የቡራዩ ከንቲባ ቢሮ እንዳሳወቃቸዉ ይናገራሉ። በዚህ ምክንያት ለሕዳር 5 ቀጠሮ ቢያዝላቸዉም ዳግም በደሕንነት ምክንያት ሙሉ በሙሉ እንደተሰረዘ አቶ በቀለ ናጋ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በእንደዚህ ጉዳይ ላይ የመንግሥት ሰልፍና ድጋፍ ካልሆነ በስተቀር የታቀዋም ፓርቲዎች እንቅስቃሴ እንደተገደበና መንግሥት በኢንቬስትመንት ስም መሬት ዘረፋ ላይ እንደተሰማራና ካዛም አልፎ አርሶ አደሮችን ተገቢ ባልሆነ ካሳ እየተፈናቀሉ መሆናቸዉን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ለዶይቼ ቬሌ ተናግሮዋል። መንግሥት የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጃ የጋራ ማስቴር ፕላኑን አስመልክቶ ከሕዝብ ጋር እንዳልተወያየና አለመወየያየቱን ምክንያት ዶክተር መረራ አስረድተዋል።
addis_ababaዶክተር ቶማስ ስቴልማን በፍር ዩንቬርስት ኦፍ ቤርልን የኤቴኖሎጅ መምህር የሆኑትና ላለፉት ከ40 ዓመት በላይ በመኅበራዊ አንትሮፖሎጂ በኦሮሞ ጉዳይ ላይ ጥናት ሲሰሩ የነበሩት ማስትር ፕላኑን አስመልክቶ የአከባቢ ነዋሪዎች ተወያይተዉበት የተስመሙ አይመስለኝም ሲሉ ገልፀዋል። ከዛም ባለፈ በአከባቢዉ ነዋሪዎች ከመብታቸዉ ደሕነት ማጣት በለፈ የቋንቋና ባህል ላይ ተፅኖ አለዉ ሲሉ ዶክተር ቶማስ ስቴልማን ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።«ስለ ማስተር ፕላኑ የሚባለው እና ያለው ስጋት፤ እስካሁን ያለው እቅድ የአድስ አበባን አከባቢ ለመቀየር የታሰበ ነዉ። ወደ ፊት የትራንስፖርት ግኑኝነቱን በምንመልኩ ይቀየር የሚል፤ የአካባቢው ሂስ ሰንዛርዎች እቅዱን እንዴት እዉን እንደምያደርጉት ምን ተግባራዊ ማድረግ እንደምፈልጉ እንኳን አያዉቁም። በሃሳብ ደረጃ አንድ ነገር አለ፣ መሰረተ ልማት ለመገንባት ታስቦዋል፣ ለዛ ደግሞ ገንዘብ ያስፈልጋል። ከዛ ማየት ነዉ የተፈለገዉ። ነገር ግን በሂደት የሚፈፀም እቅድ በፍፁም የለም።»
የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጃ የጋራ ማስቴር ፕላን በመባል የሚጠራዉን በተመለከተ እንደ አዉሮጳዉያኖች በ2014 የመጀመርያዎቹ ወራቶች አካባቢ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎች ያደረጉትን ተቃዉሞ ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች ሕይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወሳል። አሁንም ቢሆን በግልም ሆነ በፓርቲ ደረጃ በተለያዩ ቦታዎች ተቀዉሞዉ ቀጥሎዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ በኦሮሚያ ክልል መንግስት በኩል በተደጋጋሚ ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።
መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ

No comments:

Post a Comment