በገረሱ ቱፋ | September 8, 2014
አቶ ኤርምያስ ለገስ ለአስራ ሁለት አመታት የኦፕድኦ/ኢህአድግ አባል ሆኆ በተለያዩ ሃላፍነት ደረጃዎች ሲስራ ከቆየ በኃላ፣ በ2010 ወደ አሜሪካ ተሰዶ በሥልጣን ማማ ላይ የነበረበት ጊዜ “ትውስታዎቼ” ናቸው ያላቸውን በቅርቡ በመፀሓፍ መልክ አሳትሞ አሰራጭቶዋል:: ይህ “የመለስ “ትሩፋቶች” ፣ ባለቤት አልባ ከተማ” በሚል ርዕስ የታተመው መፀሓፍ በውስጡ ብዙ አጠያያቂ እና አነጋጋሪ የሆኑ ጉዳዮችን ይዞዋል:: ጊዜ ከአገኘው ወደፊት በስፋት በአጠቃላይ ይዘቱ እና ጭብጦች ላይ ሰፋ ያለ ግምገማ ለመስጠት እሞክራለው:: ለጊዘው መፀሓፉን ሳነብ ያስደመሙኝ እና በደራስው ግለሰባዊ ታዓማንነት(integrity) እንዲሁም ኢህአድግ ውስጥ የገባበት እና ውስጡ የቆየበት አላማ ምንነት ላይ አጭር ትችት ለመስጠት እሞክራልው:: ይህን ለማድረግ ያነሣሣኝ ሰሞኑን አጭር የፈሰቡክ አሰያየት ሰጥቼ ስለነበረ አንዳንድ ጏደኞቼ ሰፋ አድርጌ በሌሎች ወብሣይቶች ላይ እንድለጥፍ ስለጠየቁ ያንኑ በፈሰቡክ ላይ የለጠፈኩትን ትንሽ በማሻሻል እና በመለጠጠ ሰፋ ላለ አንባብ ለማዳረስ ነው:: ስለዝህ ይህ ትችት በውስን አንቀሶች ላይ ብቻ ነው የሚያተኩረው:: መታየት ያለብት በዚሁ ማቀፍ እንጅ እንደ አጠቃላይ የመፀሓፉ ግምገማ አይደለም::
ከላይ ለመግለፅ እንደሞከረኩት በመፀሓፉ ውስጥ ብዙ የደራስውን ግለፍሰባዊ ታዓማንነት እና ማንነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ፣አጠያያቅ የሆኑ ጭብጦች እና ሥነ አምክኖያዊ መጣረዝ የሚታይባቸው ነገሮች ተካተዋል::
No comments:
Post a Comment