Friday, April 1, 2016

አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የማህበራዊ ሚዲያዎች Block እየተደረጉ በመሆናቸው መጠቀም ያልቻላችሁ በሙሉ ይኸው መፍትሄው



የማህበራዊ ሚዲያዎች Block እየተደረጉ በመሆናቸው መጠቀም ያልቻላችሁ በሙሉ ይኸው መፍትሄው

በአቡ ዳውድ ኡስማን የተዘጋጀ አጭር የመፍትሄ ማብራሪያ
12376310_773910096075900_4723925174898218610_n
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገራችን አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዳንጠቀም እየታገደ ይገኛል፡፡ ህዝቡ በብዛት የሚጠቀምባቸው Whatsup, Viber, Tango, Telegram, Facebook Lite, Imo, Skype, etc.. ብሎክ እየተደረጉ እነዚህን አገልግሎቶች መጠቀም አልተቻለም፡፡
እነዚህን ሚዲያዎች በመጠቀም ህዝቡ የተለያዩ መረጃዎችን ለመቀባበል፣ ትምህርቶችን ለመማማር እንዲሁም የተለያዩ ጉዳዬችን በቀላሉ ለመለዋወጥ እየተጠቀመባቸው ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እነዚህ አገልግሎቶች በሃገራችን እየታገዱ በመሆናቸው አገልግሎቱ እየተቋረጠብን ይገኛል፡፡
በስልካችን ኢንተርኔት ስንጠቀም በ Operamini ብቻ ፌስቡክ እና መሰል አገልግሎቶችን መጠቀም የምንችል ሲሆን ኢንተርኔት አገልግሎት ሳይቋረጥም ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች እንደ ዋትስአፕ እና መሰል ሚዲያዎች አልሰራም እያለን ተቸግረናል፡፡ ፡፡
ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፈለጉ የሚከተለውን መፍትሄ በመጠቀም ከችግሩ በአላህ ፈቃድ በቀላሉ መላቀቅ ይችላሉ፡
መፍትሄ – 1
1. በምንጠቀምበት ስልካችን ላይ psiphon የተሰኘውን Application ከኢንተርኔት ላይ ዳውንሎድ በማድረግ መጫን
2. ይህን Application በቀላሉ በ Operamini ወይም በUc browser ማውረድ ይቻላል
3. ይህን Application ለማውረድ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ዳውንሎድ ማድረግ ይችላሉ www.apk4fun.com/int/11320/apk4fun/
4. ከላይ የተቀመጠው ሊንክ ስትጫኑ download it now from APK4Fun የሚል ምርጫ ይመጣልናል፡፡ እሱን በመጫን Application በቀላሉ ማውረድ ይቻላል፡፡
5. ይህን Application አውርዳችሁ install ካደረጋችሁ ቡሃላ ሁለት ምርጫዎችን ያመጣል፡፡ እኛ tunnel all device የሚለውን ምርጫ በመምረጥ ይህን Application መጠቀም መጀመር እንችላለን ማለት ነው፡፡
6. ይህ አፕልኬሽን ወደ ተግባር ሲገባ ሰማያዊ (Blue) P የሚል ምልክት ከስልካችን ጫፍ ላይ ያሳየናል፡፡
Grey P: connecting( ይህ ምልክት ከኢንተርኔት ጋር ተገናኝቶ ስራ ለመጀመር እየሞከረ መሆኑን ያሳየናል
Red P: not connected (ይህ ቀይ ምልክት አፕልኬሽኑ ስራ አለመጀመሩን ያሳየናል
Blue P: connected(ይህ ሰማያዊ ቀለም አፕልኬሽኑ ስራ መጀመሩን ያሳየናል
7. ይህ Application በሃገራችን የተዘጉ አፕልኬሽኖችን በሙሉ ሰብሮ በመግባት እንድንጠቀም ያስችለናል፡፡
8. ይህን Application በPlay Store ውስጥም ልናገኘው ስለምንችል ከሱ ላይ psiphon ብለን በመፈለግ ዳውንሎድ አድረገን መጠቀም እንችላለን፡፡
መፍትሄ -2
ከላይ ከተጠቀሰው Application በተጨማሪ HOLA የተሰኘ Application በስልካችን ላይ በመጫን በቀላሉ የተዘጉትን አፕልኬሽን መጠቀም እንችላለን፡፡ ይህን በቀላሉ ለመጠቀም
1. Play Store ውስጥ በመግባት HOLA ብለን በመፃፍ Search አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን፡፡
2. ይህ Application ካወረድን በኋላ ስንከፍተው በስልካችን ላይ የምንጠቀማቸውን Application ለምሳሌ Whats Up,Viber,Facebook Tango, Lite,Imo,Skype,Telegram etc.. ባጠቃላይ ሁሉንም አፕልኬሽኖች MY Apps በሚለው ምርጫ ውስጥ ተዘርዝረው ይመጣሉ፡፡
3. ሁሉንም በስልካችን ላይ የሚገኙትን Application ለማግኘት MY Apps ከሚለው ምርጫ ጎን More የሚለውን በመጫን ሁሉንም ማግኘት እንችላለን፡፡
4. ለምሳሌ Viber ከሆነ መጠቀም የፈለግነው Viber የሚለውን ስንጫን Open VIber የሚል ምርጫ ያመጣልናል፡፡ በቀላሉ Open የሚለውን በመጫን የተዘጋውን አፕልኬሽን መጠቀም እንችላለን ማለት ነው፡፡
መፍትሄ – 3
በተጨማሪም HOTSpot Sheild የተሰኘውንም Application በስልካችን ላይ በመጫን የተዘጉ ድረ ገፆችንም ሆነ አፕልኬኖች መጠቀም እንችላለን፡፡
ይህ Application በቀላሉ ለመጠቀም
1. Play Store ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ HOTSpot Sheild ብለን በመፃፍ ሰርች አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን
2. ይህ አፕልኬሽን ካወረድን በኋላ ስንከፍተው Connect የሚል ምርጫ ያመጣልናል
3. እኛ የተዘጉትን Application መጠቀም ስንፈልግ HOTSpot Sheild የሚለውን በመክፈት Connect የሚለውን ስንጫን የተዘጋውን Application በሙሉ ሰብሮ በመግባት እንድንጠቀም ያስችለናል ማለት ነው፡፡
4. ይህ Application ስራ የሚጀምረው Connect የሚለው ምርጫ ተጭነን Connected ማለቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ይህም ከስልካችን ጫፍ ላይ አገልግሎት መስጠት ሲጀመር አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ቀለም ምልክት ያሳየናል፡፡
እነዚህን Application በኮምፒውተራችንም ላይ በመጫን መጠቀም የምንችል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
በአላህ ፈቃድ ከላይ ያሉትን መፍትሄዎች በመጠቀም በሃገራችን እየተዘጉብን ያሉትን የማህበራዊ ሚዲያዎች በቀላሉ መጠቀም ያስችለናል፡፡ ከነዚህ ውጪም ሌሎች ተመሳሳይ Application ቢኖሩም በግሌ እነዚህ ጥሩ እና በቀላሉ ልንገለገልባቸው የምንችል በመሆኑ ሶስቱን እንደ መፍትሄ አቅርቤዋለው፡፡
ማሳሰቢያ፡-እነዚህን መፍትሄዎች ከኢትዬጲያ ውጪ በየትኛውም የአለማችን ክፍሎች ያላችሁም ወንድም እና እህቶች በምትኖሩበት ሃገር እነዚህን ሚዲያዎች መጠቀም እንዳትችሉ የተዘጋ ከሆነ ከላይ በተቀመጡት መፍትሄዎች በመጠቀም ችግሩን መፍታት ትችላላችሁ፡፡
ይህ ጠቃሚ ዘዴ ለሌሎች በማካፈል ከገጠማቸው ችግር እንዲገላገሉ እናግዛቸው፡፡
ሼር በማድረግ ለሌሎች እናዳርስ

No comments:

Post a Comment