የወያኔ መንግስት በህዝቦች ላይ እያደረሰ ላለው ጭቆና ፍጻሜ በማበጀት የህዝቦችን ነጻነት ለማረጋገጥ እጅ ለእጅ ተያይዞ ፍልሚያውን ከማፋፋም በስተቀር ኣማራጭ የሌለ መሆኑ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ ሊቀመንበር ኣቶ ኣብዱልወሃብ ማህዲ ኢሳ ከኦሮሞ ነጻነት ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ገለጹ።
የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ ሊቀመንበር ኣቶ ኣብዱልወሃብ ማህዲ ኢሳ ከኦሮሞ ነጻነት ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ በርካታ ጉዳዮችን ኣንስተዋል።
- የቤኒሻንጉል ህዝብ የደርግ ስርዓት በህዝቦች ትግል ተገርስሶ የወያኔ ኣምባገነን ስርዓት ስልጣኑን በሃይል ከተቆጣጠረ ወዲህም የሚደርስበት የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጭቆና እጅግ እየከፋ መሄዱን ኣቶ ኣብዱልወሃብ ገልጸዋል። በዘመነ-ወያኔ/ህወሃት ከመሬት መፈናቀልና መሰደድ እንዲሁም እስራትና ግድያ በኣስከፊ ሁኔታ በቤኒሻንጉል ህዝብ ላይ መፈጸሙን ያመለከቱ ሲሆን፡ በኣባይ ግድብ ሳቢያ የቤኒሻንጉል ዜጎች መሬታቸውን ተቀምተው ወደ ሱዳን ለመሰደድ መዳረጋቸውን ጠቅሰዋል። በዚህም ከሁዱንዱ ኣካባቢ ከ100,000 በላይ ዜጎች መኖሪያ ቤቶቻቸው ወያኔ ባሰማራባቸው ዶዘር መኪኖች ፈራርሰው መሬታቸው ስርዓቱ ከሰሜን ባመጣቸው ሰፋሪዎች መያዙና ለቻይና ባለሃብቶች መሸጡን ተናግረዋል።
- በሌላ በኩል ደግሞ በኣሁኑ ጊዜ በቤኒሻንጉል ኣካባቢ እየተካሄደ ካለው ህዝባዊ ኣመጽ በተለይም ነሃሴ 14 ቀን 2015ዓም ከተካሄደው ህዝባዊ ኣመጽ ጋር ተያይዞ የወያኔ መንግስት በርካታ ዜጎችን መግደሉንና ማቁሰሉን እንዲሁም በጅምላ ማሰሩን ኣቶ ኣብዱልወሃብ የስርዓቱ ጥቃት ሰለባ የሆኑትን የቤኒሻንጉል ዜጎች ስም ዝርዝር በመጥቀስ ኣጋልጠዋል።የኦሮሞ ነጻነትድምጽ-አማርኛ
No comments:
Post a Comment