Tuesday, May 14, 2013
ባለፉት 10 አመታት እየተስፋፋ ያለዉ በጉዲፈቻ የህፃናት ሽያጭ ብዙ ህፃናት ከሀገር እየወጡ ነዉ
የባለሞያ እና የተማረ ህብረተሰብ ስደት ለማንኛዉም ሀገር በጣም ትልቅ ጉዳት አለዉ
እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ያላደጉ ድሀ ሀገራት ላይ ደግሞ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ነዉ
የተለያዩ በየጊዜዉ የሚወጡ አለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ በዜጎች ስደት በአለም ከቀዳሚዎች ሀገራት አንዷ ነች
በየእለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በተለያዩ ምክኒያቶች ይሰደዳሉ
ለምሳሌ ያህል……
ብዙ ሴቶች እህቶቻችን በየእለቱ ለስራ እያሉ ወደ አረቡ አለም ይጎርፋሉ
ቁጥራቸዉ በግልፅ ያልታወቀ በበርሃ ወደ ኬኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት እንዲሁም ወደ ሱዳን እና ሊቢያ ይሰደዳሉ ሌሎች ደግሞ በጅቡቲ እና ሱማሊያ ወደ የመን እና ሳዑዲ አረቢያ ይሰደዳሉ
ባለፉት 10 አመታት እየተስፋፋ ያለዉ በጉዲፈቻ የህፃናት ሽያጭ ብዙ ህፃናት ከሀገር እየወጡ ነዉ
ግን አሳሳቢ እና ሀገር ሊጎዳ የሚችለዉ ቀን ከቀን እየጨመረ ያለዉ የባለሞያ እና የተማሩ ዜጎች ስደት ነዉ
ቴክኒሻን ሳይንቲስት ጋዜጠኞች ደራሲያን አስተማሪዎች ተማሪዎች ወዘተ……
“Brain drain” ወይም ማንኛዉ አይነት ስደት ምክኒያቶች አሉት
በሀገራችን ያሉት ምክኒያቶችም ..
ድህነት (poverty) በየእለቱ ያለዉ የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ዉድነት ሰዉ ከእጅ ወደ አፍ የሆነዉን ኑሮ ለማሸነፍ ለመሰደድ ይገደዳል
የስራ እድል አለማግኘት (less job opportunity or there is no right man on the right place) ለባለሞያ ወይም ለተማረዉ ተገቢ ክብር እና የሥራ እድል አለማመቻቸት
በተለያየ ጊዜ መንግስት እንደሚያዉጀዉ ባለድግሪ ኮብልስቶን ይቀጥቅጥ ብሎ አዉጇል ሥራን መናቅ ሳይሆን ባለ ድግሪ ኮብልስቶን ሲጠርብ ሚኒስተሪ ያልወሰደዉ በብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ወገናዊነቱ ብቻ ትልቅ ሥራ አስኬሀጅ ሆኖ ይሾማል (unfair)
የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የፖለቲካ አለመረጋጋት መፈናቀል ጦርነት እነዚህም ተጠቃሽ ዋና ዋና ነገሮች ናቸዉ
የበለፀጉ እና ያደጉ ሀገራት ለስልጣኒያቸዉ ዋና ምክኒያት……. ብቃት እና እዉቀት ያላቸዉን ዜጎቻቸዉን በአግባብ መጠቀም ነዉ እንዲሁም ከድሀ ሀገራት ብቃት እና እዉቀት ያላቸዉን በጥቅም ስበዉ ለሀገራቸዉ ጥቅም ላይ ማዋላቸዉ ነዉ
በተቃራኒዉ ብዙ አንጡር ሀብት ያላት አፍሪካ ለዘመናት በድህነት እና በኋላ ቀርነት ቆይታለች ከድህነት እንዳትወጣ ከምክኒያቶቹ ዋነኛዉ የተማሩ እና ብቃት ያላቸዉ ዜጎች ስደት ነዉ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment