(ለኔ ወያኔ ማለት ለአላማም ይሁን ለጥቅም የዚህን አገዛዝ እድሜ የሚያራዝም ሁሉ ነው
የወያኔን ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት
ከእስከ ነጻነት
ኢትዮጵያ የነጻነት ቀንዲል ነች፡እንደ ስበሃት ነጋ ላሉ ባንዳ
ወያኔዎች ግን ጣሊያንን አሸንፈን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነጻነት ጎህ ቀዳጅ መሆናችን ኩራት ሳይሆን እፍረት
ስለሚመስላቸው አገሪቷ ከነሰንደቅ አላማዋ ጥፍታ ማየት የዘወትር ጥረታቸው ነው፡ ሌት ተቅን የሚተጉትም ለዚህ ስለሆነ
የኢትዮጵያዊነት ሰሜት ያላቸውን ሁሉ ማሰር፤ መግደል፤ ማጥፋት ዋና ትግባራቸው ነው፡ ይህም ተግባራቸው ከበረሃ
እስከ አዲስ አበባ ከዛም ጎረቢት አገሮች ድረስ ዘልቆ አሁን ደግሞ ወደ ምእራብ ሐገራትም መጣሁ እያለ ነው።
ግን አገሪቷም ሆነ ባንዲራዋ ልትጠፋ አትችልም፡ ለጥቁር ህዝብ
የነጻነት ጎህ የቀደደች መሆኗን ለማረጋገጥ በርካታ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ሲወጡ ባንዲራቸውን መሰረት ያደረጉት
በኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ላይ ስለሆነ ባለም ዙሪያ ሲውለበለብ ይኖራል እንጂ ባንዳዎች እንደተመኙት
ልትጠፋ አትችልም።
ባለፈው አበበ ገላው ላይ የተቃጣው የግድያ ሴራ ከወያኔ
አድሎአዊ አገዛዝ፤ ሸሽተን በመጣነው ሁሉ ላይ የተቃጣ ዛቻ ነው በሚል አጠር ያለች ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅርቤ
ነበር። በዛሬው ጽሁፌ ማተኮር የምፈልገው ወያኔ (ለኔ ወያኔ ማለት ለአላማም ይሁን ለጥቅም የዚህን አገዛዝ እድሜ
የሚያራዝም ሁሉ ነው) እንዴት ተሰደን ባለንበት አገር ለማስፈራራት ብርታቱን አገኘ? እንዴትስ የወያኔ አባላት
ሰላዮች እና እበላ ባዮች በውጭው አለም በዙ? እንዴትስ መመንጠር እንችላለን የሚሉትን ዝርዝር ጉዳዮች በተመለከተ
ይሆናል።
ወደ ውጭ አገር መሰደጃ መንገዶች የታወቁ ናቸው፡ ከደርግ ጅምላ
ፍጅት ሽሽት አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ብዙ ናቸው፡ በዘር የተደራጀው እና ዘር በማጥላላትና በማጥፋተ ላይ
የተመሰረተው የወያኔ ቡድን ስርዓቱን በኢትዮጵያ ላይ ከጫነ ጀምሮ፡ ወያኔ በህዝቡ ላይ በሚያደርገው ጫና፤ ጭቆናና
ግፍ አገራችንን ለቀን ተሰደናል፡ የተሳካልን ነጻው አለም ደርስናል ያልተሳካላቸው በበረሃ አሸዋ ተውጠው ቀርተዋል፡
ባህር ውጧቸዋል፡ ከቀይ ባህር እስከ ቬንዙዌላ የውሃ ጎርፍ ወስዷቸዋል፡ ከባህር እና ካሸዋ የተረፉት በየሀገራቱ
እስር ቤቶች ተሰቃይተው ሞተዋል፡የውስጥ አካላቸው ተበልቶ ተወሰዷል፤ በእህቶቻችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን
ግፍ እና ስቃይ መናገር አይቻልም፡ የሰው ህሊና ሊያስበውና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው።
እኛስ በዚህ መልኩ ተሰደድን የወያኔ ደጋፊዎች፤ እና ሰላዮችስ እንዴት መጡ?
በስራ፤ በንግድ፤ ወይም በተለያየ መንገድ ከመጡት በተጨማሪ፡
እንደኛው ወያኔ ሊያኖረኝ አልቻለም፡ አሰረኝ፤ ገረፈኝ ብለው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው ውጭ የሚኖሩ በጣም ብዙ
ናቸው፡ በሌላም በኩል ኤርተራዊ ነኝ፡ ብለው በኤርትራውያን ስም፤ ሱማሌያዊ ነኝ ብለው በሱማሌ ስም ጥገኝነት ጠይቀው
የተፈቀደላቸው እንዳሉም ይታወቃል፡ እንዳውም የኤርትራውያንን ስደተኞች ተቀብያለሁ እና ሶስተኛ አለም ተረከቡኝ ብሎ
ሶስተኛ አገሮች ከተረከቧቸው አብዛኛዎቹ የወያኔ ደጋፊዎች እና የወያኔ ሰላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ስደተኞችን
ተቀባይ አገሮች አይወቁት እንጂ የህን ጽሁፍ በማንበብ ላይ ያለኸው፤ ያለሽው፡ ጠንቅቀው ያውቁታል።
ለምን የወያኔ ደጋፊዎች፤ ወደ ነጻው አገር መጡ አደለም
ጥያቄው፡ ይኸ መንግስት በድሎናል፤ ጨቁኖናል መኖር አልቻንም ብለው የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው፤ ጥያቄያቸው
ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ከዚሁ ጨቆነን ካሉት መንግስት ጋር አብሮ መስራት፤ የወያኔ ደጋፊዎች፤ ኢምባሲ ጭምር
በሚያዘጋጁት ስብሰባ ላይ፤ የድጋፍ ሰልፍ ላይ እንዴት ሊገኙ ቻሉ?
ይህ ብቻ አደለም ከድጋፍ አልፈው የወያኔ አገዛዝ አስመርሯቸው
የተሰደዱትን በኬንያ፤ በዩጋንዳ በሱዳን፤ በሶማሊያ፤ በጅቡቲ ሲገሉ እና ሲያሰገድሉ ኖረዋል፡ ያንን ተግበር አሜሪካ፤
ካናዳ እና አውሰትራሊያም ሊሞከሩ እንደሚችሉ፤ መገመት በቻ ሳይሆን አበበ ገላው ላይ የተጠነሰሰው ሴራና የአሜሪካው
የፌዴራል ምርምራ ቢሮ (FBI) ማክሸፉ ያላቸውን ዕብሪት በግልጽ ያሳያል።
ይህ ደግሞ በአበበ ገላው ብቻ የሚቆም አደለም ለሌሎቻችንም የሚተርፍ የወያኔ ድግስ ነው ስለዚህ እንዴት ማስቆም አለብን የሚለው ነው ቁም ነገሩ።
ይህንን ለማሰቆም ወይም የወያኔ ሰላዮችን አጋልጦ ለፍርድ
ለማቅረብ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም የሲቪክ ድርጅቶች አያስፈልጉም፡ እነሱ ወያኔን ከስሩ ለመንቀል ይንቀሳቀሱ፤ ለዚህ
ተግባር ግን የሚያሰፈልገው፡ በወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ተማረህ የተሰደድክ፡ ግፋዊ አሰተዳደሩን መቋቋም አቅቶሽ
አገርሽን ጥለሽ የወጣሽ፡ በወያኔ የግፍ ቀንበር እህትህን ያጣህ፤ ወንድምሽ እህትሽ በስደት ላይ እያሉ ባህር
የዋጠብሽ፡ አንተ ነህ፤ አንቺ ነሽ የምታስፈልጊው፤ የምታስፈልገው። በአንድ ከተማ ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ቁርጠኛ
ኢትዮጵያዊ ካለ በቂ ነው፡ በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት መከበር ጽኑ አላማ ያለውና በጥቅም ያማይገዛ ህሊና ያላቸው
አንድ ወይም ሁለት ባንድ ከተማ ካሉ በጣምበቂ ነው፡ የሚጠበቀው መደባደብ ወይም መሰዳደብ አደለም የሚያሰፈልገው
ወያኔ በድሎኛል ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ከወያኔ ቡድን ጋር እየሰራ እና ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም
ጥገኝነት የሰጠውን አገር አየስለለ መሆኑን ሪፖረት ማረግ ብቻ ነው።
ማንኛውም ሰው አንድ አገር የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቅ በስልጣን
ላይ ያለው መንግስት በደለኝ ብሎ መኖር አልቻልኩም ካለና ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ በሗላ ያ መንግስት
እስካልተቀየረ ድረስ ከዛ መንግሰት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሊኖረው አይችልም፡ በምንም መልኩ ከዛ መንግስት ጋር
ግንኙነቱን ከቀጠለ ከመንግስቱ ጋር ችግር የለበትም ማለት ነው ስለዚህ ወዳገሩ መመለስ አለበት፡ የኽ የኔ
አስተያየት ሳይሆን የየሃገራቱ የስደተኛ ህጎች ናቸው።
ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ
የተፈቀደለት፡ ወይም ኤርትራዊ፤ ሶማሊያዊ ነኝ ብሎ ጥገኝነት የተፈቅደለት (ወንድ ይሆን ሴት፤ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤
ትገሬ ይሆን አደሬ፤ ማንም ይሁን ማ) የወያኔው ኢምባሲ በሚያዘጋጀው ፕሮገራም ላይ የሚሳተፍ፤ የወያኔ ባለስልጣናት
በሚጠሩት ስብሰባ ላይ የሚገኝ፤ የወያኔ ደጋፊዎች ወይም ካደሬዎች በሚያዘጋጁት የወያኔ የድጋፍ ሰልፍ ላይ የሚገኘን፡
ከወያኔ ጋር የንግድ ስራ ጀምሮ ኢትዮጵያ የሚመላለስን ሁሉ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ማደረግ ያስፈልጋል።
ባለፈው 21 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት አልተቀየረም
ስለሆነም በነዚህ ጊዜያት የወያኔ መንግስት በድሎኛል፤ ሊያኖረኝ አለቻለም ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሰው ሁሉ
በምንም መልኩ ከወያኔ ጋር የሚሰራ፡ ወያኔ በሚያዘጋጀው ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሁሉ ሪፖርት መደረግ አለበት።
እዚህ ላይ አደራ የምለው እና ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው
ሪፖርት የሚደረገው ነገር እውነት ብቻ እንዲሆን፤ በግል ቂም በቀል፤ ወይም በተወሰነ ዘር ላይ ያነጣጠረ እንዳይሆን
አደራ እላለሁ፡፡ ወያኔን ያጠናከረው፡ የተወሰነ ዘር ወይም የወያኔው አባላት ብቻ ሳይሆን እበላ ባይ አጃቢ ጭምር
መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡ ስለዚህ ሁሉም የወያኔን እድሜ እየለመነ የወያኔን ፍርፋሪ የሚለቃቅም ሁሉ ሪፖርት
መደረግ አለበት።
ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ከወያኔ ጋር መደባደብ መነታረክ ሳይሆን ሰማቸውን ቢቻል አድራሻና ፎቶገራፋቸውን መዝግቦ መያዝ ነው ከዛ ለሚመለከተው ረፖርት ማድረግ።
ሪፖርት ለማድረግ የግድ የግል ሰማችሁን መጠቀም አይኖርባችሁም፤
ሰሜ አይገለጽ ማለትም ትችላላችሁ፡ ከቤታችሁ ሪፖረት መላክ ካላመቻችሁ ወይም ካልፈለጋችሁ ከህዝብ መጻሕፍት ቤት
ኮምፑተር ተጠቅማችሁ ሪፖርት ማድርግ ትችላላቸሁ፡ የህዝብ ቤተ መጻህፍት አባል ለመሆን ክፍያ አይጠይቅም ነጻ ነው፤
የሚጠይቀው መታወቂያ ወይም ባደራሻችሁ በስማችሁ የተላከ ደብዳቤ ብቻ በቂ ነው፡
መልክታችሁ አጭር ነው፡
“እገሌ የሚባል ሰው አዚህ አገር ሲገባ መንግስት ጨቆነኝ
አላኖር አለኝ፤ ብሎ ነበር አሁን ግን ጨቆነኝ ከሚለው ከመንግስት ጋር በቀጥታ እየሰራ ስለሆነ ሰላይ ሊሆን ይችላል
ወይም የጥገኝነት ጥያቄው የውነት አደለም ብዬ እጠራጠራለሁ ማጣራት ቢደረግ”
ማጣራቱ የናንተ ጉዳይ ሳይሆን የደህንነት ሰራተኞች ጉዳይ
ይሆናል፡ ከማንም ሳትማከሩ፤ አዩኝ አላዩኝ ብላችሁ ሳትፈሩ፤ ሚስጥሬ ይባክናል የሚል ስጋት ሳይኖራችሁ ትክክለኛውን
መረጃ ለሚመለከተው ክፍል መስጠት የህሊና ነጻነት መጎናጸፍ እና የዜግነት ድርሻን መወጣት ነው፡
ሪፖርት የምታደርጉባቸውም አድራሻዎች
No comments:
Post a Comment