ሰበር ዜና፣ በባህር ዳር ከተማ ከ16 በላይ ሰዎች ተገደሉ
እሁድ
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ የአባይን ድልድይ እንዲጠብቅ የተመደበ የፌደራል ፖሊስ አባል እያነጣጠረ ሰዎችን ሲገድል
አምሽቷል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ16-18 ንጹሀን ዜጎች ያለምንም ምክንያት ከፌደራል ፖሊሱ በተተኮሱ
ጥይቶች ተገድለዋል።
የፌደራል ፖሊሱ እያነጣጠረ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል በአቅራቢያው የነበሩ የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበው እንደቆዩ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ህይወት ሊታደጉ ሲገባቸው ይልቁኑም ሰውየውን ለመያዝ በመፈለግ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ግለሰቡ ያገኘውን ሰው እየተኮሰ ሲገድል እንደነበር በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል።
ሁኔታው በባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ መረበሽ መፍጠሩ ታውቋል። የከተማው ነዋሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የተካሄደውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለማውገዝ እንደሚፈልጉም ዜናውን ያቀበሉን የባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በበኩሉ ዜናውን እንዲህ ዘግቦታል)
http://www.youtube.com/watch?v=_L1Wnd8Ifcg&feature=player_embedded#!

No comments:
Post a Comment