Thursday, June 20, 2013

በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ፊትለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ነው ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያውንን ጩሀት ሰምቶ መልስ እንደሚሰጥ ተናገሩ

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያውያን ለመብታቸው መከበር የሚያሰሙትን ድምጽ ይሰማል ሲሉ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ተናገሩ


ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል የሆኑት እና በምርጫ 97  ወቅት የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ  የነበሩት ወ/ሮ አና ማርያ ጎሜዝ ይህን የተናገሩት ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ፊትለፊት  ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ  ነው ። ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያውንን ጩሀት ሰምቶ መልስ እንደሚሰጥ  ተናግረው፣ በግላቸው ከኢትዮጵያውያን ጎን ቆመው  ለውጥ እስከሚመጣ  እንደሚታገሉ ተናግረዋል።
በተቃውሞው ላይ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ውስጥ እየደረሰ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዘርዝረው ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት አቅርበዋል።
ከተቃውሞ ሰልፉ አዘጋጆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ሻውል ሰልፉ የተሳካ እንደነበር ገልጸዋል።

1 comment:

  1. Good job! if any one has Anna Gomez contact address esp. her e-mail ID, you are kindly reuested to send me by kerimfek@yahoo.com,
    Thanks and victory for our people and beloved mother land!!!!!

    ReplyDelete