Sunday, June 23, 2013
የአባይ ወንዝ ሕዳሴ ግድብ፣ ለማንና ለምን ጥቅም? June 23, 2013
June 23, 2013
የዚህ
ጽሑፍ አላማ፣ ስለ አባይ ወንዝ ግዙፍ ግድብ ስራ አጭር ምርምር ለማቅረብ ነው። ስለግድቡ እጅግ ብዙ ትችት
ተሰጥቶበታል፤ አሁንም እየጎረፈ ነው። ስለ ዕቅዱ አስፈላጊው ጥናት መካሄዱ አይታወቅም። ጥናት ተደርጎ ከሆነ ውጤቱን
ሕዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም። ስራውን በልዩ መልክ የሚቆጣጠር ልምድ ያላቸውንና የታወቁ ባለሙያዎችን ያካተተ
ባለስልጣን አካል አልተፈጠረም። ለተነሱት ጥያቄዎች አወዛጋቢ እንጂ ትክክለኛ መልሶች አልተሰጡም። ሌሎችም ውዥግቦች
ታክለው የግድቡ ስራ በውጥንቅጥ ሃሳብ ተጸንስሶ በሚያጠራጥር ደረጃ ቆሟል። አንድ የልማት ስራ ሲታቀድ፣ በልማድ
ወይም እንደ ሀገሩ ህግ በግዳጅ፣ በፍጥረትና በተፈጥሮ ላይ በቀጥታ ወይም በተዘዋሪ መንገድ ስለሚያመጣው ተጽዕኖ
“ስለአካባቢው ፍጥረት ተጽዕኖ ምርምር” (ኢንቫየሮንሜታል ኢምፓክት እስቴትሜንት (EIS)” የተባለ ጥናት አስቀድሞ
ይካሄዳል። የግድቡ ስራ ለሕዝብ ይፋ የሆነው በድንገት ጠቅላይ ምንስትር (ጠ/ም) መለስ ዘናዊ መሰረተ ድንጋይ
ሲያስቀምጡ ነው። ግድቡ ለኢትዮጵያ ጥቅም ተብሎ ታስቦበት የተወጠነ መሆኑን የሚያመለክቱ ነገሮች የሉም። በአስቸኳይ
የግድቡ ስራ መጀመሩ፣ ግራ የተጋባው ሕዝብ ጥያቄ በመጠየቁ ‘ጸረ ብልጽግና’ በመባል ተኮንኗል። ግድቡ ከፍተኛ ወጭ
የሚጠይቅ ግዙፍ ስራ ስለሆነ፣ ጉዳቱም ለሀገርና ለሕዝብ እንዲሁ ከፍ ያለ ስለሚሆን፣ ባለሙያዎች የግድቡን ስራ
እንዲመረምሩ ይገደዳሉ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment