Wednesday, June 19, 2013

የኢትዮጵያውያን የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን በአትላንታ ተቋቋመ፣ ዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን ምስረታ

June 19, 2013
Alemtsehay Breast Cancer Foundation (ABCF)
info@abcfonline.org * abcfonline.org
facebook.com/ABCancerFoundation

ቅዳሜ፣ ሰኔ 15፣ ቀን 2013 ዓም በአትላንታ ከተማ “የዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን” (Alemtsehay Breast Cancer Foundation) መመሥረቱን ወ/ሮ ፊፊ ደርሶ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አስተዋውቀዋል። የፋውንዴሽኑም የመጀመርያ ስብስባ የተደረገው በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማዕከል ነበር። በስብሰባው የተገኙት ተሳታፊዎች በአትላንታና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ስለፋውንዴሽኑ መመስረት እጅግ መደሰታቸውንና ሙሉ በሙሉም ድጋፋቸውን የሚለግሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከተሰበሰቡት መካከል 3ቱ ከካንሰር ህመም የዳኑ (survivors) መሆናቸውን ሲናገሩ፣ “ድርጅቱ አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን አስረድተዋል። በዋና ተናጋሪነት የተጋበዙት ወ/ሮ ለምለም ጸጋው ከዋሽንግተን ዲሲ ነበሩ።Fifi Derso, announced the creation of Alemtsehay Breast Cancer Foundation (ABCF) in Atlanta.
ፋውንዴሽኑ የሚቀጥሉትን አገልግለቶች ለመሥጠት አቅዷል፤
1. በአሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንደ እድሜያቸው የሚደረገውን የጡት ምርመራ በራሳቸውና በሃኪሞች እንዲመረመሩ ማስገንዘብ፣ በሽታውም ይዟቸው በህክምናም ላይ ካሉ የመንፈስም ሆነ የገንዘብ ድጎማ እርዳታ መለገሥ፥
2. በአሜሪካ ለሚገኙ በጡት ካንሰር ለተያዙ ኢትዮጵያውያንና ቤተሰቦቻቸው ደጋፊ ማህበር (support group) ማቋቋም፥
3. በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ሴቶች ስለበሽታው ምንነትና ምን ማድረግ እንድሚችሉ፥ ህክምናም ሆነ ትምህርት ስለበሽታው ሴቶችም ሆኑ ወንዶች እንዲያገኙ፣ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በተለያዩ ሃኪም ቤቶችና የጤና ጣቢያዎች በመተባበር መሥራት፥
4. በአሜሪካ አገር ካንሰርን ለማጥፋት ለሚረባረቡ ድርጅቶች ስለኢትዮጵያውያን ሴቶች ለምርመራም ይሁን ህክምና ለማግኘት ያለባቸውን ችግር አስረድቶ ድጋፍ እንዲሰጡ መጣር፥
5. ስለጡት ካንሰር ጥናት የሚያደርጉትን ተቋማት በአሜሪካ የሚኖሩ በጡት ካንሰር የተያዙ ኢትዮጵያኖችን ቁጥር ለይተው እንዲመዘግቡ መገፋፋት።

One Response to የኢትዮጵያውያን የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን በአትላንታ ተቋቋመ፣ ዓለምፀሐይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን ምስረታ

No comments:

Post a Comment