ግብፅ የታላቁ የህዳሴ
ግድብ ጉዳይ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር
በረከት ስምኦን ገለፁ፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ግብፅ የግድቡን የሃይል
ማመንጨት አቅም መቀነስ እንደመፍትሔ ማቅረቧ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር አቶ በረከት ስሞኦን
ግብፅ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የግንባታ ሂደቱ 22 ነጥብ 5 በመቶ የደረሰውና በተያዘው ዓመት
26 በመቶ ስራው እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብን አስመልክቶ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የያዙት አቋም
ትክክል አለመሆኑንም ሚኒስትር በረከት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር በረከት አያይዘው እንደገለፁት ግብፅ ጉዳዩን የውስጥ
የፖለቲካ ችግሯን ለማርገብ እየተጠቀመችበት መሆኑን ጠቅሰው ሀገሪቱ የጦርነት አማራጭ የተዘጋ አይደለም ትበል እንጂ
ወደዚህ ተግባር ትገባለች ተብሎ አይጠበቅም ብለዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው የጦርነት
አማራጭ እንደማያዋጣ የተገነዘበ የሚመስለው የግብፅ መንግስት የህዳሴን ግድብ የማመንጨት አቅም፣ የሚይዘውን የውሃ
መጠንና ከፍታ እንዲቀንስ የሚያነሳው የመፍትሔ ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ ህዳሴ
ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር በረከት ስሞኦን እና የውሃና ኢነርጂ
ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮና በ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በህዳሴው ግድብ ወቅታዊ
ጉዳዮች ዙርያ ባተኮረው የቀጥታ ውይይት ላይ በአገር ውስጥና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያሳዩት ያሉትን ግድቡን
የመገንባት ቁርጠኝነትና ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሃላፊዎቹ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ (ምንጭ፤ ኢሬቴድ)
ፓርላማው የቅኝ ግዛት ዘመን ውል የሚተካ አዲስ ህግ አፀደቀ
አሥራ አንዱ የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ ፣
ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ ናቸው፡፡ የተፋሰሱ አገራት
በተመለከቱበት ካርታ ላይ ደቡብ ሱዳን አልተካተተችም። ካርታው ሲሰራ ደ/ሱዳን በወቅቱ ነጻ አገር አልነበረችም
ነበር።
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ33ተኛው መደበኛ
ስብሰባው ከመከረባቸው አምስት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እንዳፀደቀ
የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ከኢትዮጵያ በስተቀር አምስቱ አገሮች ማለትም የርዋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያና የቡሩንዲ ፓርላማዎች ቀደም ብለው ውሉን ያፀደቁት መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል።
የኢንቴቤ ስምምነት እየተባለ የሚጠራው ውል ቅኝ ገዢ በነበረችው
ታላቋ ብሪታኒያ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም የተረቀቀና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰስ አገሮች
ይልቅ ለግብፅ ሙሉ መብት የሚሰጠውን ውል የሚተካ መሆኑ ይታወቃል።
ውሉ ዛሬ በኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ሰሞኑን
በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ከሚካሄደው ውዝግብ ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሕዝብ
ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል፡፡(ምንጭ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)
በአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ
ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል።
መንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ
ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት በአስችኳይ ወደ
አካባቢው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። በፌደራል ፖሊስ ሲደረግ የነበረው ጥበቃ በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲጠናከር
ያደረገው መንግስት ፣ በሻለቃ አበራ ወረታው አዛዥነት የሚመራው የምእራብ እዝ የ44ኛ ዳሎል ክፍለ ጦር አራተኛ ሪጂመንት በቤንሻንጉል እንዲቀመጥ ተወስናል።
በደቡብ ሱዳን ያለው ጦር የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኝም
አብዩታዊ ዴሞክራሲ እና ወታደራዊ አመራር የሚል ርእስ ያዘለ የመወያያ ጽሁፍ ተዘጋጅቶ በ ስልጠና ዋና መምሪያ
ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመራ ቡድን ወደ አብየ አቅንቷል፡፡
ኢሳት የደረሱትን ሙሉ ወታደራዊ የደህንነት መረጃዎች ለአገር
ደህንነት ሲባል ይፋ ከማውጣት መቆጠቡን ለመግለጽ ይወዳል። የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ኢትዮጵያ
ምንም አይነት ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች አይደለም በማለት ሰሞኑን መግለጫ ቢሰጡም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ
እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን ኢትዮጵያ ግድቡን ከጥቃት ለመከላከል እንቅስቃሴዎችን ጀምራለች።
በሌላ ዜና ደግሞ የግብጽ መንግስት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ
የማሸሻያ እርምጃ እንድታደርግ መጠየቁ ታውቋል። የግብጽ መንግስት ያቀረበው ጥያቄ የግድቡ ከፍታ ከነበረበት 145
ሜትር ወደ 100 ሜትር ዝቅ እንዲል፣ 74 ቢሊዩን ሜትር ኩብ ውሃ እንደሚይዝ የሚጠበቀው አዲሱ ሀይቅ ከ 32
እስከ 40 ቢሊዩን ሜትር ኩብ ውሀ እንዲቀንስ መጠየቁን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የሀይል አቅርቦቱም ወደ
3000 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ የግብጽ መንግስት ጥያቄ አቅርቧል። (ምንጭ፤ ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት
ዜና)
ለአማራው መፈናቀል ተጠያቂ የተባሉ 2 የቤኒሻንጉል ም/ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ተነሳ
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ።
ያለ
መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ የተደረገው በክልሉ ከማሺ ዞን የዞኑ ዋና
አስተዳዳሪ አቶ መለተጊ ቦጋለና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊው አቶ ገርቢ በጊዜው ናቸው።
እነዚህ አመራሮች የክልሉ መንግስትና ፓርቲው በማያውቀው ሁኔታ በዞኑ ያሶ ወረዳ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸው በመረጃ በመረጋገጡ ነው እርምጃው የተወሰደባቸው።
በዚህ የማፈናቀሉ ተግባር ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 18 የሚደርሱ ከቀበሌ እስከ ዞን የሚገኙ አመራሮች ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል።
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ
ይስሀቅ አብዱልቃድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በማጣራት ባአሁኑ ጊዜ
ተፈናቃዮች ተረጋግተው ወደቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ኑሮዋቸውን እያከናወኑ ነው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2005
(ኤፍ.ቢ.ሲ)
“ዋነኛው የእንግልት ሰለባ አህያው ነው”
ፖሊስና እርምጃው በግንቦት 30 እትሙ በምስራቅ ሸዋ መቂ ከተማ
ውስጥ አንድ ግለሰብ ጅብ አጥምዶ ፤ ከማጥመዱም በአህያ በሚጎተት ጋሪ ጭኖ ሲዘዋወር በመገኘቱ ‹‹እንሰሳትን
በማንገላታት›› ክስ መታሰሩን ነግሮናል፡፡
ሰውየው ‹‹ጅቡን ከነነፍሱ ያጠመድኩት እየተፋፋመ ያለውን የፀረ ሙስና ትግል መቀላቀሌን ለማሳየት ነው›› ካላለ በስተቀር ትንሽ በቁጥጥር ስር ሳይቆይ አይቀርም፡፡
‹‹እንሰሳትን በማንገላታት›› የሚለው ክስ እንግልቱ በየትኛው እንሰሳ ላይ እንደተፈፀመ አጥርቶ ባይገልፅም፤ እንደኔ በዚህ ጉዳይ ዋነኛው የእንግልት ሰለባ አህያው ነው፡፡
መደበኛ የሸክም እንግልቱን ተዉት፡፡ ይህ አህያ ታሪካዊ አዳኙን/ ጠላቱን ከነነፍሱ ተሸክሞ ሲዞር ‹‹ካሁን አሁን ዘነጠለኝ›› እያለ መሳቀቁ ብቻ ከባድ የስነልቦና እንግልት አይደለም?
ይህን ጅቦችን ተሸክመው ሲሄዱ የኖሩ ምስኪን አህዮች ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡
ወጣም ወረደ፤ ክሱ ጅቡን የእንግልቱ ተጠቂ አድርጎ ያቀረበ መሆኑን ከሰማን ‹፣ድሮም የኛ ሕግ ለጅቦች ያዳላል›› ማለታችን የማይቀር ነው፡፡
(ምንጭ፤ ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር – Hiwot Emishaw)
No comments:
Post a Comment