Sunday, April 7, 2013

ማፈናቀሉ እስከመቼ?

ስራት ወልደሚካኤል

ህወሓት/ኢህአዴግ በህይወቱ ከሚፈራውና ከሚጠላው ነገር አንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ማየትና መስማት ነው፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ አባላት በባህሪያቸው በውሸት፣ በተንኮልና በዕውቀት አስተሳሰብ አድማስ ደካማ ስለሆኑ የዜጎችን አንድነትና ብሔራዊነት ስሜትን አጥብቀው ይጠላሉ፤ ይህንንም በማሰራጨት የማሃይሞችን ርካሽ ፖለቲካ አራምደውበታል፣እያራመዱም ይገኛሉ፡፡ የዚህ ዋነኛ ተባባሪ ደግሞ በህወሓት የሚነዱት ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የሀገሪቱን አንድነትና ደህንነት አደጋ ላይ በመጣላቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዝምታ ሊያልፍ ስለማይገባ እስካሁን ለፈፀሙት ሁሉ አስፈላጊውን ሰነድ በእጃችን ማስገባት፣ ድርጊቱን የፈፀሙትንና ተባባሪዎቹን ስም ዝርዝር ከነ ሙሉ አድራሻቸው መያዝ፣ ጉዳት የደረሰባቸውና ሚደርስባቸው ዜጎችን መርዳትና መንከባከብ እንዲሁም ወንጀለኞችን በተለያዩ ማኀበራዊ ሚዲያዎች(Facebook, blog, twitter,….) ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በማጋለጥ ለህግ እንዲቀርቡና ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን የውዴታ ግዴታ መሆን ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ዛሬ በሰፊው የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ በህወሓት/ኢህአዴግ እየደረሰ ያለው ግፍ በተመሳሳይ መልኩ ነገ በሌሎችም ላይ ይደርሳል፤ ከዚህ በፊትም ደርሷልና፡፡
ስለዚህ በቅርቡ በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ለረጅም ጊዜ ሀብት ንብረት አፍርተውና ተዋልደው የኖሩ የአማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀል ስራ የተሰራውን መረጃ በሚመለከት ፣
አሁን ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ለሞት.ለስቃይና ለመከራ እንዲደረጉ የተደረገበትን ምክንያት በዝርዝር በማጣርት መረጃውን ይፋ በማድረግ ሁሉም ዜጋ በጋራ ሊያወግዝና የተፈናቀሉትም ወደነበሩበት ስፍራ በክብር እንዲመለሱ ለማድረግ በሀግር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለዚህም በሀገር ውስጥ ያሉ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ወደስፍራው በመሄድ አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ መረጃውን ለህዝብ ይፋ ማድረግና የድርጊቱ ፈፃሚዎችም በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ፣
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ይህን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በማጋለጥ ለኢህአዴግ የሚደረገው የለጋሾች ድጋፍ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚውል ማረጋገጥና ድጋፉ እንዲቋረጥ ከማድረግ በተጨማሪ መረጃውን ለሚሰበስቡ ሀገር ውስጥ ላሉ ሀገር ወዳድ ሰባዓዊ ባለሙያዎች የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የሙያ ድጋፍ ማድረግ፣
በተለይ ወንጀሉ የሚፈፀምባቸው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖቻችን ወኪል ነኝ የሚለውን ብአዴን/ኢህአዴግ አባላት ጉዳዩን አጥብቀው በመጠየቅ ለድርጅቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ በማቋረጥ ለህዝብ እና ለሀገር ያላቸውን ወገንተኝነት ማረጋገጥ፣ ከፓርቲውም በይፋ በመልቀቅ ህዝባዊ ዓላማ ያለውን ትግል መቀላቀልና የወንጀል ተባባሪ አለመሆናቸውን በተግባር በማሳየት ከነገ ተጠያቂነት እራሳቸውን ነፃ ማድረግ፣
የሌላው ማኀበረሰብ ኢትዮጵያዊያን ድርጊቱን በጋራ በማውገዝ አሁን እየተፈፀመ ያለው ዘግናኝና አሰቃቂ ወንጀል ወደ ሌሎችም መዛመቱ ስለማይቀር “ማፈናቀሉ እስከመቼ?” በሚል ሁሉም በጋራ በመንቀሳቀስ በራሱ ተስፋ የቆረጠውን ዘረኝነት አገዛዝ እርቃኑን በማስቀረት ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን በማፅናት የዜጎች ሰብዓዊ መብት በሙሉ መከበሩን ለማረጋገጥ የዜጎች ከሀገራቸው መፈናቀል፣ መሰደድ፣ በግፍ መታሰርና መገደል ማብቃት አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ ነገ ሁላችንም ከሀገራችን መፈናቀላችን አይቀሬ ስለሆነ ዛሬውኑ ቆም ብለን በማሰብ ማድረግ ያለብንን መወሰን ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ማንም ኢትዮጵያዊነታችንን ሲፈልግ ወስዶ እንካችሁ፤ ሳይፈልግ ዜግነታችሁን እኔ የምሰጣችሁ ስፍር ብቻ ነው ሲሉ መፍቀድ ባርነትን ከመምረጥ ውጭ ምን ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን? እኔ በበኩሌ ባርነትን በፍፁም አልመርጥም፣ አልደግፍምም፡፡

ማፈናቀሉ እስከመቼ?

ስራት ወልደሚካኤልህወሓት/ኢህአዴግ በህይወቱ ከሚፈራውና ከሚጠላው ነገር አንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ማየትና መስማት ነው፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ አባላት በባህሪያቸው በውሸት፣ በተንኮልና በዕውቀት አስተሳሰብ አድማስ ደካማ ስለሆኑ የዜጎችን አንድነትና ብሔራዊነት ስሜትን አጥብቀው ይጠላሉ፤ ይህንንም በማሰራጨት የማሃይሞችን ርካሽ ፖለቲካ አራምደውበታል፣እያራመዱም ይገኛሉ፡፡ የዚህ ዋነኛ ተባባሪ ደግሞ በህወሓት የሚነዱት ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የሀገሪቱን አንድነትና ደህንነት አደጋ ላይ በመጣላቸው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዝምታ ሊያልፍ ስለማይገባ እስካሁን ለፈፀሙት ሁሉ አስፈላጊውን ሰነድ በእጃችን ማስገባት፣ ድርጊቱን የፈፀሙትንና ተባባሪዎቹን ስም ዝርዝር ከነ ሙሉ አድራሻቸው መያዝ፣ ጉዳት የደረሰባቸውና ሚደርስባቸው ዜጎችን መርዳትና መንከባከብ እንዲሁም ወንጀለኞችን በተለያዩ ማኀበራዊ ሚዲያዎች(Facebook, blog, twitter,….) ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን በማጋለጥ ለህግ እንዲቀርቡና ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን የውዴታ ግዴታ መሆን ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ዛሬ በሰፊው የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ላይ በህወሓት/ኢህአዴግ እየደረሰ ያለው ግፍ በተመሳሳይ መልኩ ነገ በሌሎችም ላይ ይደርሳል፤ ከዚህ በፊትም ደርሷልና፡፡
ስለዚህ በቅርቡ በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ለረጅም ጊዜ ሀብት ንብረት አፍርተውና ተዋልደው የኖሩ የአማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀል ስራ የተሰራውን መረጃ በሚመለከት ፣
አሁን ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ለሞት.ለስቃይና ለመከራ እንዲደረጉ የተደረገበትን ምክንያት በዝርዝር በማጣርት መረጃውን ይፋ በማድረግ ሁሉም ዜጋ በጋራ ሊያወግዝና የተፈናቀሉትም ወደነበሩበት ስፍራ በክብር እንዲመለሱ ለማድረግ በሀግር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ለዚህም በሀገር ውስጥ ያሉ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ፖለቲከኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ወደስፍራው በመሄድ አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ መረጃውን ለህዝብ ይፋ ማድረግና የድርጊቱ ፈፃሚዎችም በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ፣
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ይህን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ በማጋለጥ ለኢህአዴግ የሚደረገው የለጋሾች ድጋፍ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚውል ማረጋገጥና ድጋፉ እንዲቋረጥ ከማድረግ በተጨማሪ መረጃውን ለሚሰበስቡ ሀገር ውስጥ ላሉ ሀገር ወዳድ ሰባዓዊ ባለሙያዎች የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የሙያ ድጋፍ ማድረግ፣
በተለይ ወንጀሉ የሚፈፀምባቸው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኖቻችን ወኪል ነኝ የሚለውን ብአዴን/ኢህአዴግ አባላት ጉዳዩን አጥብቀው በመጠየቅ ለድርጅቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ ሙሉ ለሙሉ በማቋረጥ ለህዝብ እና ለሀገር ያላቸውን ወገንተኝነት ማረጋገጥ፣ ከፓርቲውም በይፋ በመልቀቅ ህዝባዊ ዓላማ ያለውን ትግል መቀላቀልና የወንጀል ተባባሪ አለመሆናቸውን በተግባር በማሳየት ከነገ ተጠያቂነት እራሳቸውን ነፃ ማድረግ፣
የሌላው ማኀበረሰብ ኢትዮጵያዊያን ድርጊቱን በጋራ በማውገዝ አሁን እየተፈፀመ ያለው ዘግናኝና አሰቃቂ ወንጀል ወደ ሌሎችም መዛመቱ ስለማይቀር “ማፈናቀሉ እስከመቼ?” በሚል ሁሉም በጋራ በመንቀሳቀስ በራሱ ተስፋ የቆረጠውን ዘረኝነት አገዛዝ እርቃኑን በማስቀረት ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን በማፅናት የዜጎች ሰብዓዊ መብት በሙሉ መከበሩን ለማረጋገጥ የዜጎች ከሀገራቸው መፈናቀል፣ መሰደድ፣ በግፍ መታሰርና መገደል ማብቃት አለበት እላለሁ፡፡ አለበለዚያ ነገ ሁላችንም ከሀገራችን መፈናቀላችን አይቀሬ ስለሆነ ዛሬውኑ ቆም ብለን በማሰብ ማድረግ ያለብንን መወሰን ያለብን ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ማንም ኢትዮጵያዊነታችንን ሲፈልግ ወስዶ እንካችሁ፤ ሳይፈልግ ዜግነታችሁን እኔ የምሰጣችሁ ስፍር ብቻ ነው ሲሉ መፍቀድ ባርነትን ከመምረጥ ውጭ ምን ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን? እኔ በበኩሌ ባርነትን በፍፁም አልመርጥም፣ አልደግፍምም፡፡

የቆራሄ ጀግና አፈወርቅ ወልደ ሰማያት የፋሺስት ኢጣልያን ጦር የመከተ


ከዓለማየሁ አበበ ሽንቁጥ
(የቀድሞ አምባሳዳር)

ቤኒቶ ሙሶሉኒ ሀሙስ ማታ በ12 ሰዓት ላይ መስከረም 22 ቀን 1928 ዓ.ም. ከጽሕፈት ቤቱ ሰገነት ብቅ ብሎ በመቆም ንግግሩን ለመስማት ይጠባበቅ ለነበረው ለመላው የጣልያን ሕዝብ “ኢትዮጵያን ለ40 ዓመታት ታገስናት እንግዲህስ በቃ” ብሎ ረጅም የድንፋት ንግግር ሲያደርግ የሕዝቡ ደስታ እጅግ በጋለ መልኩ ይስተጋባ ነበር:: ይህም በተንቀሳቃሽ የፊልም ምስል በዓለም ዙሪያ ታይቷል፡፡ ለአገራቸው ተቆርቁዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በቁጭትና በንዴት ይመለከቱታል፡፡ ይቀጥላል…

 http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6871

Tuesday, April 2, 2013

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት!

አቤ ቶኪቻው
መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆችReeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner. አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤
ከአንድ ወር እስከ አራት ወር ለሚደርስ ጊዜ በወዳጅ ዘመዶቿ እንዳትጎበኝ፤ ደብዳቤ እንዳትልክ እና እንዳትቀበል (ይሄ እንኳ አሁንም ተግባራዊ ተደርጎባታል) የእስር ቤቱን ቤተ መጻህፍት እንዳትጠቀም፣ በእስር ቤቱ በሚደረግ የጋራ ዝግጅት እና መዝናኛ ላይ እንዳትሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ለሚደርስ ጊዜ ለብቻ እስር ትዳረጋለች፡፡
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ያቺ በቃሊቲዊቹ ውቃቢ ትፈቀድ የነበረች አመክሮም ልትከለከል ነው ማለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤልም በእስር ቤቱ እየደረሰበት ያለውን አበሳ በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላትም ቅጥ ያጣውን የእስር ስርዓት ሃይ ለማለት የርሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
ወይ ጣጣ… ብዬ የራሴን አስተያየት በአዲስ መስመር አቀርባለሁ…
እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምነው እንዲህ መካሪ አጣ…? እርሱ እኛን በስንቱ መከራ እንዳልመከረን እርሱን የሚመክረው ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡
እስቲ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እስሩ አንሶ አሳር የሚያበላው ምን ይሁነኝ ብሎ ነው? እንደሰማነው በርካታ የህሊና እስረኞች በታመሙ ጊዜ የሚያክሟቸው የእስር ቤቱ ሀኪሞች “መግደል ነበር አንተን” “መጨረስ ነበር አንቺን” እያሉ ያስፈራራሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ይሄ የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውና ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ መንግስታችን “ባትሪ ሎው” እያለ ይመስለኛል!

- የሳውዲ መንግስት “ህገ ወጦችንና በህጋዊ ሸፋን ህግን ጣሱ” የሚባላቸውነን የውጭ ዜጎች ለማጥራት የተጀመረው ቀጣይ ዘመቻ

Asif Asim
ዜና ሳውዲ
- የሳውዲ መንግስት “ህገ ወጦችንና በህጋዊ ሸፋን ህግን ጣሱ” የሚባላቸውነን የውጭ ዜጎች ለማጥራት የተጀመረው ቀጣይ ዘመቻ ወደ ሁለት ሚሊዮን ነዋሪዎች ከሃገር እንደሚበረሩ በሳውዲ መገናኛ ብዙሃን በኩል ይገመታል. . . – ዘመቻው በዋና ከተማዋ በሪያድ ፣በጅዳ ፣ደማምና በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል- 130 ሸህ የሚደርሱ በሴት ሳውዲ ስም የተመዘገቡ ትናንሽና መካከለኛ ድርጅቶች በማጠራቱ ሂደት ይነካሉ . . .-ስጋት ያደረባቸው ርካታ ድርጅቶች እየተዘጉ ነው ፣ ያለአሰሪያቸው የሚሰሩትም ስራ እያቆሙ ነው. . .- የበርካታ ሀገር ቆንስላና ኢንባሲዎችዜጎቻቸውን ለጥንቃቄ በማማከር ላይ ሲሆኑ የአደጋ ጊዜ ግንኙነት የሚፈጥሩባቸውን መስመር ሳይቀር በማቅረብ ላይ ናቸው- ይህ ዘመቻ ኢትዮጵየውያን ህጋዊ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል ! የኢናባሲና ቆንስል ምስሪያ ቤቶች ሊመክሩ ሊዘክሩም ሆነ መረጃ ሊያቀብሉ አልጠሩንም ! ሳይታሰብ ከቤተሰቡ ሊያፈናቅል የሚችል ዜጋ ስል በሰደት ሰላፈራው ሃብት ንብረትና ቤተሰብ ደህንነት ጠበቃ የመቆም ማነው? ለምንስ ቆንስልና ኢንባሲ አስፈለገን?

የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት?

ስለ ኦነግ ሲነሳ አብዛኞች በመገረም የሚናገሩትና ሚዛን የሚደፋው አስተያየት የሚሰነዘረው በድርጅቱ መከፋፈልና መበጣጠስ ሳይሆን ተለያይተውም አስመራን የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ህጻን እያለ ሻዕቢያ እንዳሻው ይነዳው እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች ከሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ኦነግ አገር ለቆ እንዲወጣ መንገዱን የጠረገው ሻዕቢያ መሆኑንን በቁጭት ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ለስልጣን አዲስ በሆነበት የጨቅላነት ዘመኑ፣ ኦነግ በታሪኩ ያልነበረውን ሰራዊት በመገንባት አስጨንቆት እንደነበር በመጠቆም በወቅቱ አስተያየት የሰጡ ኢህአዴግ በተለይም መለስ በሻዕቢያ በኩል ኦነግን ለመታረቅ አቅርበውት የነበረውን የሽምግልና ጥያቄ ኦነግ እንዳይቀበል ሰሚ ባያገኙም በአጽዕኖት ምክራቸውን ሰጥተው ነበር።
በኦነግ ታጣቂ ሃይሎችና በኢህአዴግ ሰራዊት መካከል እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የጡንቻ መፈታተን ነበር። ደርግ ሲበታተን ኦነግን የተቀላቀሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አካላት ወያኔን የማዳፋት አቅሙ ነበራቸው። በወቅቱ የንስር ያህል ጉልበትና ሃይል ቢኖራቸውም ራሳቸውን ጫጩት አድርገው ተመለከቱ። አዲስ አበባ ሲገቡ የነበራቸውን የህዝብ ድጋፍ አራግፈው ጣሉት። በስሜት እየተነዱ ከሚወዷቸው ሁሉ ተቀያየሙ። ህወሃት አጋጣሚውን ለቅስቀሳና ለስም ማቆሸሻ ሰራበት። በስተመጨረሻ ኦነግ ሃይሉንና አቅሙን ዘንግቶ በአመራር ችግርና በአቋም ሸውራራነት ሃይሉን በሙሉ ወደ ካምፕ በማስገባት የኢህአዴግን የእርቅ ጥያቄ ተቀበለ። ሰራዊቱን እየነዳ በፈቃደኛት አሳሰራቸው።
በሻዕቢያ አደራዳሪነት ሁርሶ፣ ደዴሳና መስኖ የገባው ሰራዊት “በደባ” ተከቦ ትጥቁን እንዲፈታ ተደረገ። አብጦ የነበረው የኦነግ ጡንቻ በቅጽበት ከሰመ፤ ሰለለ። ኦነግ ሲቆጣጠራቸው የነበሩትን ቦታዎች ለማስተዳደርና በኦህዴድ ለመተካት ኢህአዴግ እንደ እባብ ተሹለክልኮ ዓላማውን አሳካ። ሻዕቢያም በዚሁ ውለታው ኢትዮጵያንና ኢኮኖሚዋን ብሎም የኢትዮጵያን ስነልቦና እንዳሻው እንዲጋልብ ተፈቀደለት። ብዙ አሻጥር ተፈጠረ፤ ተፈጸመም። ደንዳና ቆዳ ያላት ኢትዮጵያና ህዝቧ ተቦጠቦጡ። ተዘረፉ። አንድ እግር የቡና ተክል የሌላት ኤርትራ ቡና ላኪ ከሚባሉት ቀዳሚ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተሰለፈች። አፈርን።
“አገሬን ከወራሪ አጸዳሁ” በማለት ከበሮ እየመታ ጦርነት አልቋል ብለው እጅ የሰጡ የወገን ወታደሮችን የረሸነው ሻዕቢያ ኢትዮጵያንም ያስተዳድር ጀመር። ዛሬ የሚማልባቸውና “ውርሳቸውን ሳናዛባ እናስጠብቃለን” የሚባልላቸው አቶ መለስ እንደ ባዕድ መሪ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም ለሻዕቢያ አሳልፈው ሰጡ። የሻዕቢያ ታጣቂዎችና ኢትዮጵያ አብልታ ያሳደገቻቸው ጎረቤቶቻችን ሳይቀሩ ናጠጡብን። በየደጃቸው መሳሪያ ወደላይ እየተኮሱ በደስታ ውለታ ባስቀመጠችላቸው አገር ላይ ተሳለቁ። ምስኪኖችን ቤት እያስለቀቁ ወረሱ። የሌላቸውን ሃብትና ንብረት ሰበሰቡ። በኤርትራ ምድር በግፍ ለተረሸኑ የኢትዮጵያ ልጆች ተከራካሪ ጠፋና የሞት ሞት ሞቱ። አገራችን የግፈኞች መፈንጫ እንድትሆን መለስ በበረገዱት በር የገባው ሻዕቢያ ከርሱ ሲጎድል፣ “ልክህን እወቅ” የሚሉ ሲነሱ፣ ስርዓት ያዝ ሲባል ደሙ ተንተከተከና የሃይደር ህጻናትን በጠራራ ጸሃይ በላቸው። ትግራይን ወረረ። ሲሰርቁ ኅብረት የነበራቸው ሲከፋፈሉ ተጣሉና አገር ውርደት ገባው።
ይህንኑ ተከትሎ አገር አልበቃ ብሏቸው የነበሩና ወያኔን ሲያገለግሉ የነበሩ ቅጥረኞች የሰበሰቡትን ሳይበሉ ወደ “ከባርነት ናፅነት” ብለው ድምጻቸውን ወደሰጡላት “እናት አገራቸው ኤርትራ” ተጋዙ። ንብረታቸውን በትነው አገር ለቀው ወጡ። ከነጻነት በኋላ “ታይላንድ ትሆናለች፣ ሲንጋፖር ትሆናለች፤ ሆንግኮንግ ትሆናለች” በተባለላት አገራቸው ለመኖር ተገደዱ። ዳቦ ተሰልፈው ለመግዛት ታደሉ። ኬክ በለመደው፣ ቁርጥ በቆርጠው፣ “ሹካ ባስለመደው” እጃቸው ይድሁበት ገቡ። ወታደር ሆኑ። የሰገዱለትና ቅጥረኛ ሆነው ያገለገሉት ህወሃት መልሶ በረሃ በተናቸው። የሚያሳዝነው ግን ኤርትራዊያን ከየመንደሩ ተለቅመው ወደ አገራቸው ሲሄዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አውቶቡስ ከብበው ደረት እየመቱ ያለቅሱላቸው ነበር። ደብቀው ያስቀሩዋቸውም አሉ። ጨርቃቸውን ጥለው አውቶቡስ እንዳይነሳ በፍቅር አምላክ የተንፈራፈሩ ነበሩ። ሁኔታውን የሚያስታውሱ ድርጊቱን “የሞኝ” ተግባር አድርገው ሲወሰዱት ሌሎች ደግሞ “ክፉ ላደረገብህ ክፉ አትመልስ” የሚለው ግብረገብነት የገባቸው የፈጸሙት የጀግንነት ተግባር ነው በማለት የአዲስአበባ ነዋሪዎችን የመንፈስ ልዕልና ያደንቃሉ፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት ጀምሮ ኦነግ ሻዕቢያን ሲለማመነውና እግሩን ሲልሰው የኖረ ድርጅት ዛሬ ድረስ ተበጣጥሶም እዛው አስመራ አምልኮ ደጅ ይገኛል። ከአመት ዓመት ያለ ለውጥ እዛው ይንፏቀቃል። እንደሚሰማው ከሆነ ወታደሮቹ የሻዕቢያ አግልጋዮች ሆነዋል። አመራሮቹም ቢሆኑ አስመራን ለቀው የመውጣትና እንዳሻቸው የመንቀሳቀስ መብት የላቸውም። በዚህም ይሁን በሌላ መነሻ ኤርትራ በከተሙት የተለያዩ የኦነግ ሃይሎች ላይ ከያቅጣጫው ስሞታ መቅረብ ከጀመረ ሰንብቷል። ኤርትራን ለቀው መውጣት አለባቸው የሚለው የኦሮሞ ልጆች ድምጽም በርክቷል። ጥያቄው አያሌ ፖለቲካዊ ማብራሪያ የሚጠይቅና አማራጭ መፍትሄ የሚያሻው ቢሆንም ኤርትራ ውስጥ አሉ በሚባሉ ታጣቂ ተቃዋሚዎች ያልተማረሩና ያልተሰላቹ ቢኖሩ አፍቃሪ ሻዕቢያዎች ወይም ራሳቸው የሻዕቢያ ሰዎች ወይም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሻዕቢያን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ብቻ ናቸው።
እንግዲህ በዚህ መሃል ነው አስመራን ተሳልመው ከነበሩት የኦነግ አመራሮች መካከል አቶ ሌንጮ ለታ፣ አቶ ዲማ ነገዎና ሌሎች ሰሞኑን አዲስ ዜና ይዘው ብቅ ያሉት። አዲስ ፓርቲ በማቋቋም ድፍረት የተሞላው አቋም በማራመድ “አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ ለመመስረት ተነስተናል። የቀድሞው የትግል ስልት አያዋጣም” ያሉት። ሃሳቡ መልካም ቢሆንም እንዴት? የሚለው ጥያቄ የበርካቶች ነው። ምክንያቱም በግልጽ “የቀጣዩ ትግል ሜዳ አገር ቤት ነው፤ አገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ተብሏልና!
“የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” ODF የሚባል አዲስ ግንባር መቋቋሙ ከአሜሪካ የሚኖሶታ ጠቅላይግዛት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች እየተወረወሩ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጥርት ያለ መልስ አልተሰጠም። ግንባሩ መመስረቱ ይፋ ከሆነ በኋላ መጋቢት 22፤2005ዓም (ማርች 31/2013) በዚያው ጠቅላይግዛት በሚኒያፖሊስ ከተማ በተካሄደ ስብሰባ አንዳንድ ጉዳዮች ይፋ ሆነዋል።
ከብሪታንያ፣ ስዊትዘርላንድ፣ ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያ፣ ከጀርመንና ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ቁጥራቸው 400 የሚጠጋ ተሰብሳቢዎች ባካሄዱት ውይይት አስፈላጊ የተባሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል። ኢትዮጵያን “ኢምፔሪያሊዝም፣ ቅኝ ገዢና ጠላት” አድርገው በመሳል ጥያቄ የሰነዘሩትን ጨምሮ ስለ ቀጣዩ ትግል ትግበራና ሰለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር በስፋት ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሌንጮ ለታ አስገራሚ መልስ ሰንዝረዋል።
“ያለፈውን በመውቀስ የትም አንደርስም። አሁን ማየትና ማሰብ ያለብን ወደፊት ነው። ሌሎች ወገኖችን አግልለን ብንታገል የትም አንደርስም። ያለፈው የትግል መንገድ ስህተት ነበር” ብለዋል። ስለ ኦሮሞ ህዝብ ነጻነት መከበር ሲናገሩ “የሁሉም ኢትዮጵያዊ መብት ካልተከበረ የኦሮሞ መብት ብቻውን ሊከበር አይችልም” በማለት መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
“ጊዜው ተለውጧል። ጊዜው አዲስ ነው። አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው” በማለት የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ “አገር ቤት እንዴት ገብቶ መታገል ይቻላል?” በሚል ለተነሳው ጥያቄ የሰጡት መልስ አዲሱን ድርጅታቸውንና እርሳቸውን የሚፈትን እንደሆነ ያመላከተ ነው።
ቀጣዩ ትግል ኤርትራ ላይ እንደማይሆን በግልጽ የተናገሩት አቶ ሌንጮ፣ አገር ውስጥ በመግባት ለማደራጀት፣ ለመታገል፣ ለመንቀሳቀስ ይቻል ዘንድ “መንገድ እንፈልጋለን” ብለዋል። ኢህአዴግ በተደጋጋሚ እንደሚለው ለድርድር የሚቀመጡ ወገኖች መጀመሪያ ህገመንግስቱን መቀበልና ህግመንግስቱን አክብሮ ለመስራት መማል አለባቸው። ይህ ወደፊት የሚታይ ቢሆንም አገር ቤት ለመግባትና ለመታገል እነ አቶ ሌንጮ ቢስማሙ እንኳን ሌላ መሰረታዊ ችግር እንዳለ ከወዲሁ እየተጠቆመ ነው።
በኦሮሞነታቸው በሚያነሱት ጥያቄ እስር ቤት የታጎሩ የኦሮሞ ልጆች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው – በአስር ሺዎች እንደሚቆጠር ይገመታል። በየቦታው ባሉ እስር ቤቶች ዋናው የመግባቢያ ቋንቋ ኦሮሚኛ እስከመሆን የደረሰበት ሁኔታ ነው የሚታየው። ይህ እውነታ ባለበት አቶ ሌንጮ የሚመሩት አዲሱ ድርጅት እንዴት አድርጎ ይታገላል? ወይም ደግሞ አባላቶቹ እስርና እንግልት እንዳያጋጣማቸው ምን ዓይነት ማረጋገጫና መተማማኛ ማግኘት ይቻላል?
“መልሱ ግልጽ ነው” በሚል ይመስላል “የፈለገው ቢመጣ፣ አስፈላጊው ህግን የጠበቀ ትግል ይካሄዳል። አገሪቱ ላይ ያለውን ህዝብ አስሮ ይችል እንደሆነ የሚታይ ይሆናል” የሚል እንደምታ ያለው ምላሽ ነው እየተሰነዘረ ነው ያለው። በሌላ በኩል አገር ቤት ገብቶ መታገል ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ ሲወሰድ አዲሱ ጉዳይ የቀድሞው ሌሎችን ሲያገልና “ልዕልናና ነጻነት ለኦሮሞ ብቻ” በሚል የፖለቲካ ሾፌር ሲደወር የነበረው የትግል ስልት መቀየሩ ነው። በዚህም የተነሳ ይመስላል “ከማናቸውም በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ መረጋገጥና ለህዝብ እኩልነት ከሚሰሩ ድርጅቶችና ፓርቲዎች ጋር አብረን እንሰራለን። የቀድሞው መንገድ አይዋጣም” የሚል ምላሽ የሰጡት።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ “እኔን ተከተል፣ ስትቃወም ከኔ ቀመር አትዛነፍ” የሚለውን አመለካከት ጨምሮ በድፍን የአንድ እንቅስቃሴ እርግጠኛ መነሻ ሳይታወቅ አስቀድሞ “የማብከትና የማበስበስ” ስራ መስራት የተለመደ በመሆኑ ከሁሉም ወገን እርጋታ እንደሚጠበቅ፣ ረጋ ብሎ መመርመር እንደሚያስፈልግ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ላለፉት 20 ዓመታት ኢህአዴግ በብሄር እየለየ በፈጠረው ገደል እየተወረወሩ የሚገቡ ፖለቲከኞች በሰሩት ጥፋት ህዝብ ለከፍተኛ የአእምሮ ጉዳት ተዳርጓል። ኢህአዴግ የ50 ዓመት የቤት ስራ እንደሰጠ አድርጎ የሚያስበውም እነዚሁ የፖለቲካ መሪዎች የህወሃትን የሳሳ ፖለቲካ መረዳት ባለመቻላቸውና ከዋናው ጠላታቸው ይልቅ እርስ በርስ ለመቧቀስ የፈጠኑ መሆናቸውን በቀላሉ ስለሚያሳዩት ነው።
ከ40 ዓመታት የስህተት ጉዞ በኋላ አገር ቤት በመግባት “ሁሉም ነጻ ካልወጡ ኦሮሞ ብቻውን ነጻ አይወጣም” በሚል የትግል መርህ መነሳት በራሱ አስደሳች እንደሆነ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል በስልክ ባደረጉት አጭር ቃለምልልስ ተናግረዋል።
“ድንበርና ክልልን ሳይሆን የምንጋራው አብሮነትን ነው” ያሉት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “በዲኤንኤ ምርመራ ጎሳ አይታወቅም። ተመሳሳይ ዲኤንኤ ያላቸው ጎሳዎችም የሉም። ሁሉም ነጻ ካልወጡ ማንም ነጻ እንደማይወጣ መስማት ታላቅ ብስራት ነው” በማለት ከዓመታት ትግልና ውትወታ በኋላ ድርጅታቸው ሲታገልለትናሲሟገትለት የቆየው ዓላማ የሌሎችም መርህ ሆኖ በማየታቸውና በመስማታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብላጫውን ቁጥር የሚይዘው የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ዓይነቱ መርህ ለዘመናት የቆየው ሥርዓቱም ሆነ አኗኗሩ ቅርብ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አመልክተዋል፡፡ ድርጅታቸው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” በሚል የከበረ መመሪያ ላይ ሲሰራ መቆየቱን የገለጹት አቶ ኦባንግ ከዚህ መመሪያ በተጨማሪ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም” በሚለው የትግል መርህ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡ ይህንን መፈክር አሁን ደግሞ ኦሮሞ ወገኖቻችን ሲያነሱ መስማት ለድርጅታቸው ታላቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ላይ ማንም ሳይጠራቸው በራሳቸው አነሳሽነት እንደሄዱ ያስታወቁት አቶ ኦባንግ “የኦሮሞ ተወላጆች ስብሰባ ሲቀመጡ የሚነጋገሩት ስለ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝና ውይይቱ ይመለከተኛል። ስለዚህ ተገኘሁ። በደስታ ተቀበሉኝ። በስብሰባው ውስጥ በሰማሁት አዲስ ሃሳብ ተደሰትኩ” ብለዋል።
ላለፉት 20 ዓመታት አንዱ ስለ ሌላው ሲያወራ መኖሩን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ አሁን አንድ ላይ በመሆን ለመመካከርና “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ” ግንባታ በጋራ ለመታገል መወሰን ከልምድ የተገኘ የፖለቲካ ተሃድሶ መሆኑን አስታውቀዋል። አያይዘውም ድሮም ቢሆን ፖለቲከኞች እንጂ ህዝብ አእምሮ ውስጥ ያልነበረ አስተሳሰብ በማቀንቀን ለህወሃት ፖለቲካ ማዳበሪያ የማቅረብ ስራ ሲሰራ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ ሌንጮ ለታ እንጀምረዋለን ያሉት አዲሱ መንገድ ሁሉንም ህዝብና የፖለቲካ ድርጅቶች ማዕከል በማድረግ ለመስራት ወስኖ የተነሳ እንደሆነ ሲያስታውቁ ያሰመሩበት ጉዳይ ቢኖር “ያለፈውን አናስብም። አሁን አዲስ ምዕራፍ ላይ ነን። አዲሱ ምዕራፍ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተያይዘው የሚፈጥሯትን አዲስ አገር ማየት ነው፡፡” እርሳቸው እንዳሉት 40 ዓመት ባክኗል። አሁንም መንቃት አግባብ ነው። ነገር ግን ድጋፉም ሆነ ተቃውሞው በተራ የድጋፍና ተቃውሞ ስሜት ሳይሆን ረጋ ብሎ በመመርመር እንደሆነ የሚመክሩ ጥቂቶች አይደሉም።
(ፎቶዎቹን የወሰድነው ከ Hegeree Media channel ቪዲዮ ላይ ነው)

Saturday, March 16, 2013

አራት የኦሮሞ ድርጅቶች ነገ በሚኒሶታ ቀጣይ የትግል ራዕያቸውን ያሳውቃሉ


ዘ-ሐበሻ) በኦሮሞ ሕዝብ ቀጣይ የትግል ጉዞ ላይ ለመወያየት በሚል የተዘጋጀውና ሁሉንም የኦሮሞ ድርጅቶች ያሳተፈው ኮንፍረንስ ነገ ቅዳሜ ማርች 16 ቀን 2013 በሚኒሶታ እንደሚደረግ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።
ራሱን የ’ኦሮሞ-አሜሪካውያን ሲትዝን ካውንስል” በሚል የሚጠራው ተቋም ባዘጋጀው በዚህ ትልቅ ኮንፈረንስ ላይ በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ፣ በኦቦ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዲያሎግ ፎረም፣ በኦቦ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኃይል ተወካዮች እና ጃዋር መሐምድ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
በዚህ ስብሰባ ላይ ለመገኘትም ኦቦ ሌንጮ ለታና ጃዋር ሙሐምድ ሚኒሶታ እንደገቡ ታውቋል።
የኦሮሞ ሕብዝ ትግል ቀጣዩ ጉዞ በሚል በተዘጋጀው በዚህ ኮንፈረንስ ላይ የተጋበዙት ድርክቶች ድርጅቶች ለኦሮሞ ሕዝብ ቀጣይ የትግል አካሄድ ያላቸውን ራዕይ እንደሚያስረዱ ይጠበቃል። በጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ትክክለኛው ፌደራሊዝም የሚተገበርባትን ኢትዮጵያ ለመፍጠር እንደሚታገል ቀድሞ ያሳወቀ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ድርጅቱን ወክለው የሚቀርቡት ኦቦ ቃሲም አባነሻ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላም በኩል አዲስ የትግል ራዕይ ይዞ የመጣው የኦሮሞ ዲያሎግ ፎረም በኦቦ ሌንጮ ለታ በኩል ወደፊት ስለሚከተለው የትግል ራዕይ በተለም በተለያዩ ዓለማት እየተዟዟረ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር በጋራ ታግሎ ወያኔን መጣል እንዳለበት ሲያስረዳና ሲወያይበት የነበረውን ጉዳይ ያብራራል ተብሎ ይጠበቃል።
የተበተነው የጥሪ ወረቀት የሚከተለው ነው፤ ዘ-ሐበሻ የዚህን ስብሰባ ውጤት ተከታትላ ትዘግባለች።
zehabesha.com