Friday, January 29, 2016

የኦሮሞን ሕዝብ ትግል ከመጠራጠር ይልቅ


አድ አዳማ
freedomበኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ አሁንም ተቀጣጥሎ በቀጠለበት በአሁኑ ሰአት በሌላው የኢትዮዽያ ክፍል ግን አልፎ አልፎ ጎንደር ላይ ከሚሰማው ውጥረት በስተቀር ይህ ነው የሚባል ምንም አይነት የአመፅ እንቅስቃሴ አይታይም። በተለያዩ ሚዲያዎች ወይም ድሕረ ገጾች ሌሎች ክልሎች ሕዝባዊ አመፁን እንደሚቀላቀሉና በኦሮሞ ህዝብ ያለዉ ጥያቄ በሌሎች ክልሎችም እንዳለና አንድ ቀን ሊፈነዳ እንደሚችል ሲነገር ቆይቷል ነገር ግን እስካሁን አመርቂ የሆነ እንቅስቃሴ በሌሎች ክልሎች የተደረገበት ሁኔታ የለም። አንዳንድ ከኦሮሚያ ክልል ውጪ ያሉ ፖለቲከኞች እንደሚሉት ከሆነ ሌላው ክልል አመፁን ያልተቀላቀሉበት ምክንያት በትግሉ ላይ ጥርጣሬ ስላላቸው ፣ ወይም አንድ ፀሀፊ እንዳስቀመጡት በኦሮሚያ እና በአካባቢዋ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ሌሎች ክልሎች ያልተቀላቀለበት ምክንያት በኦሮሞ ሕዝባዊ አመጽ ውስጥ የማያምኑት ንጥረ ብሔርተኝነት አለ ወይም ይኖራል ብለው በመፍራታቸው ነው። ስለዚህ ትግሉ Oromo Protest የሚለው Ethiopian Protest በሚለዉ መቀየር ይኖርበታል ይላሉ። ሌላው ደሞ በተለይ ስለ ርዕሰ መዲናዋ ፊንፊኔ ወይም አዲስ አበባ ሲነሳ አምስት ለአንድን መደራጀት እንደትልቅ ምክንያት ይጠቀሳል ነገር ግን ሁለቱም ምክንያት ውሃ የማይቁዋጥሩ ናቸው።
አምስት ለአንድ ከሚለው ከሁለተኛው ምክንያት ልነሳ። አምስት ለአንድ የሚባለው የስለላ መረባቸውን ፋሺስት TPLF በመላው ኢትዮዽያ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ነገር ግን እንኩዋን የተማረው ያልተማረው ጀግናው የኦሮሞ ገበሬ አፈራርሶ ከጥቅም ውጪ አድርጎታል። ጉዳዩ ምንም የተለየ ሚስጥር የለወም ይህ ከታች ያለውን ምስል እንመልከት። ይች የምታዩዋት ፈረስ በመጀመሪያ ሰሞን ጠንካራና የማይነቃነቅ ግንድ ላይ ነበር ስትታሰር የቆየችው አሁን ግን አንድ ፕላስቲክ ወንበር ላይ ታስራ ሳትንቅሳቅስ እንደ ድሮው ጠንካራና የማይነቃነቀው ግንድ ላይ የታሰረች መስሏት ቆማለች። ይህ የሚያመለክተው የዚህች ፈረስ የታሰረው አእምሮዋ እንጂ አካሏ አይደለም። ስለዚህም የአዲስ አበባ ህዝብ ያልተነሳው የአምስት ለአንዱ አደረጃጀት ጥንካሬ ሳይሆን በውስጡ ባለው አላስፈላጊ የሆነ ጥርጣሬ እና ፍራቻ ነዉ። አምስት ለአንዱን እናፍርስ ከተባለ የሚያስፈልገው ቆራጥነትና ዋጋ መክፈል ብቻ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ወያኔዎች ልጆቹን በገደሉበት ወቅት ቀብሮ ዝም ብሎ ወደቤቱ አልተመለሰም ይልቁንም ሞት አያቆመንም በማለት የቀብሩን ስነስረዓት እየቀየረ የተቁዋሞ መድረክ እያደረገው አመጹን ቀጥልዋል። ለውጥ ለማምጣት መስዋት መሆን የግድ ነው ብሎም ያምንል።
አሁን ደግሞ ትግሉ ብሔርተኝነት በውስጡ አለ በሚል ሌሎች ብሔሮች በጥርጣሬ ያዩታል ስለዚህ ትግሉ Oromo Protest የሚለው Ethiopian Protest ወደሚለው መቀየር ይኖርበታል ወደሚለው ልመለስ። በመጀመሪያ ደረጃ የ25 አመቱ ግፍና መከራ አንገሽግሾት አመጹን ያለምንም ማመንታት ውድ ልጆቹን መሰዋእት በማድረግ ከሁለት ወራቶች በላይ እያካሄደ ያለው የኦሮሞ ሕዝብ ነው። ስለዚህ Oromo Protest የሚለው የአመፁ መጠሪያ ብዙም የሚያከራክር አይደለም። ሲቅጥል 45 ምሊዮን ከሚሆን ህዝብ አንድ አይነት አመለካከት ብቻ መጠበቅ የለየለት ሞኝነት ይመስለኛል። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ እየሞተ ትግሉን በቀጠለበት ወቅት ሌላው ህዝብ የችግሩ ተጠቂ ሆኖ ዝምታን ሲመርጥ ብሄርተኝነት በተቁዋሞ ውስጥ መንፀባረቁ የሚገርም አይሆንም።
ትግሉን ከOromo Protest ወደ Ethiopian Protest መቀየር ከተፈለገ የቀረዉ ሕዝብ እንደ ኦሮሞ ሕዝብ መነሳት በቂ ይናሆል። እዚህ ጋር ሌላው ሕዝብ ለመነሳት የኦሮሞ ሕዝብ ትግል አጋር መሆን ወይም መቀላቀል ሳይሆን የሚያስፈልገው የራሳቸውን ችግር ማንሳት ብቻ በራሱ ከበቂ በላይ ነው። የትኛውም ክልል ወይም ብሔረሰብ በወያኔ መራሹ የወንበዴ ጥርቅሞች ላይ ለመነሳት እልፍ አእላፍ የሆኑ ከበቂ በላይ ምክያቶች አሉት። እስቲ ለአብነት ያህል ልክ እንደ ኦሮሚያው ለህዝባዊ እምቢተኝነት የሚያበቁ ምክንያቶችን በስፋት ሕዝባዊ ተቃውሞ ይነሳባቸዋል ተብሎ የሚጠበቁ የተወሰኑ ክልሎች ወስደን እንመልከት። በመጀመሪያ አማራ ክልል ቀጥሎ ደሞ ርዕሠ መዲናዋን ከዚያ ጋምቤላ ወስደን እንመለከታለን።አሁንም ወያኔዎች የሚያደርሱት ልክ የሌለው የ25 አመቱ ግፍና በደል እንዳለ ሆኖ ልክ ከኦሮሚያ ክልል ተነጥቆ ለአዲስ አበባ ሊሰጥ እንደነበረው ወልቃይት በሀይል ወደ ትግራይ አልተካለለም፧ ዋልድባ ገዳም በግፍ ለኢንቨስተሮች አልተሸጠም፧ ከሁሉ የሚብሰው ደሞ ከጎንደር ሰፊ መሬት ተነጥቆ ለባዕድ ሀገር ሱዳን ለመስጠት ወያኔ የካርታ የማንሳት ስራዋን እያጠናቀቀች አይደለምን፧ ካሉት አያሌ ምክንያቶች ለህዝባዊ እንቢተኝነት እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ከበቂ በላይ ናቸው።
አዲስ አበባ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ በአንድ ቀን ከ 200 የሚበልጡ ዜጎችዋን አጥታ ደም ዕንባ አላነባችም፧ ነጋዴ በግፍ ከገበያ ሲስተም እንዲወጣ አልተደረገም፧ በአረብ ሀገር ግፍና በደል ለደረሰባቸው ወገኖች ሰልፍ የወጡ ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች አልተቀጠቀጡም፧ በሊብያ በአሸባሪዎች ለተቀሉት ወገኖች መንግስት እራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ዜጎች በአደባባይ የዱላ ውርጅብኝ አልወረደባቸውም፧ የጋምቤላ ህዝብ ከመሬቱ በኢንቨስትመንት ስም አልተፈናቀለምን፧ የጋምቤላ ክልል ከ400 በላይ ዜጎቹን አጥቶ የፍርድ ያለህ አያለ እየጮኸ አይደለምን፧ ኡጋዴን ሲዳማ እያልን ብንቀጥል ለሕዝባዊ አመፅ የሚያበቁ በርካታ ምክንያቶች አሉ።
ታዲያ ይሄ ሁሉ መከራና ስቃይ እየደረሰበት ሌላው ብሔረሰብ ያለመነሳቱ ሚስጥር ምን ይሆን፧፧፧ ልክ ፀሀፊው እንዳስቀመጡት በኦሮሚያ እና በአካባቢዋ የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ የሌላ ብሄረሰብ ሰዎች (በይበልጥም አማራው ) ያልተቀላቀለበት ምክንያት በዚህ በኦሮሞ ሕዝባዊ አመጽ ውስጥ የማያምኑት ንጥረ ብሔርተኝነት አለ ወይም ይኖራል ብለው በመፍራታቸው ከሆነ ገና ለገና የኦሮሞ ብሔርተኝነትን በመፍራት አማራው ለመብቱ መከበር ላይነሳ ነው፧ ወልቃይትንም አሳልፎ ሊሰጥ ነው፧ ሁሉም ይቅር የጎንደር መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ሲሰጥ ዝም ብሎ ሊመለከት ነው፧ እምቢተኝነቱ በጥርጣሬ ታየ አልታየ የኦሮሞ ሕዝብ ከመቼውም በላይ ጥንካሬውን እያሳየ ተቃዉሞውን ሳያቁዋርጥ ወደፊት እየገፋ ነው። ዋናው ነገር እዚጋ የኦሮሞ ህዝብ እምቢተኝነት ፣ ብሔርተኝነት ይኑረው አይኑረው የሚወሰነው በሕዝቡ ነው። ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ እንቢተኝነት በውስጡ ብሔርተኝነት አለበት ከማለት ይልቅ ሱዳን ድንበራን አካላ ሕጋዊ ከማድረጉዋ በፊት ወያኔ የማካለሉን ስራ ተግባራዊ እንዳታደርግ የአማራው ሕዝብ ሌላውን በማስተባበር ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን ከዳር እስከዳር አንቀሳቅሶ ልክ እንደ ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ እንዳይሆን ማስቆም አለበት።
አድ አዳማ (Norway)

No comments:

Post a Comment