Sunday, February 8, 2015

የተገደሉ የኦሮሞ ዜጎች ቁጥር የትየለሌ ነው።

 By afomia yosef
የወያኔ ኣምባገነን መንግስት የፖለቲካ ስልጣኑን በሃይል ከተቆጣጠረ ኣንስቶ ባሉ 23 ዓመታት ውስጥ ይህን በመሰለ ዘግናኝ ሁኔታ የተገደሉ የኦሮሞ ዜጎች ቁጥር የትየለሌ ነው። የወይኔ ስርዓት የኦሮሞ ምሁራንና የህዝብ ኣለኝታ የሆኑ የኦሮሞ ዜጎችን በኦነግ ኣባልነት ወንጅሎ የመሰወር ያረጀ-ያፈጀ ስልት  ዘግናኝና ኢ-ሰብዓዊ ሰቆቃ ሲፈጸምበት ነበር።  በማዕከላዊ፣በቃሊቲ፣በቂሊንጦና በዝዋይ እስር ቤቶች ውስጥ የወያኔ መንግስት የኦሮሞልጆችን ኣፍኖ ካሰረና የከፋ ሰቆቃ ከፈጸመባቸው በኋላህይወታቸው ልታልፍ ስትል ኣንገታቸው ላይ ገመድ በማንጠልጠል እራሳቸውን እንደገደሉ በማስመሰል እንዲሁም ታመዋል በሚል ለይስሙላ ሃኪም ቤት መውሰድና የመሳሰሉትን በመጠቀም በኦሮሞ ልጆች ደም የጨቀየውም እጁን ንጹህ ለማመሰል እያደረገ ያለው ጥረት የኦሮሞ ህዝብን ሊያሞኝ እንደማይችል ያስገነዝባል የወያኔ መንግስት በተደጋጋሚ የኦሮሞ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን ይህንን ድርጊትም በጽኑ ያወግዛል።እንዲህ ባለው እስነዋሪ ተግባርና ኢ-ሰብዓዊ እርምጃ ህዝቡን ለማንበርከክ ወያኔ እየተጠቀመበት ላለው ስልት ሳይንበረከክ የኦሮሞ ህዝብ ትግሉን ኣፋፍሞ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት ኣስተላልፋኣለው።

No comments:

Post a Comment