Saturday, October 4, 2014

ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ለነጻነት ንቅናቄ ወቅታዊ አቋም

Qeerroo
ከሕዝባችን ነጻነት የቀደማ አንዳችም ጉዳይ የለም!
የትግላችን ጅማሬዉናፊጻሜዉ ፣ መነሻዉና መድረሻዉ ፣ዉጥኑናግቡ – ሁለነገሩ የሕዝባችንን ነጻነትማረጋገጥ ነዉ።ይህ የሕዝባችን ነጻነትሺዎች የተሰዉለት፣ሚሊዮኖች የሚዋደቁለት፣ኣእላፍ የታሰሩላትናየሚሰቃዩለትአሁንም ሚሊዮኖች ለገቢራዊነቱ  የሚሻሙበት  ታላቅ ዓላማ ነዉና ከሕዝባችን የነጻነት አጀንዳ የቀደማ ኣንዳች ጉዳይ የለንም -የሕዝባችን ነጻነትከምንምና ከማንም የላቃብቸኛጉዳያችን   ሆኖ እስከፊጻሜዉ ይቀጥላል።
የኦሮም ሕዝብ ከተወራራሽ ወራሪ ኃይሎች አገዛዝ ተላቆ ብሔራዊ ነጻነቱ ና ሰብዓዊክብሩ እስክረጋገጥድረስ ፤እንድሁም የኦሮሞ ነጻነትና የኦሮሚያ ሉዓላዊነት ዕዉን ሆኖብሔራዊ ሰንደቁ በዓለም ለይ ተገቢዉን ስፍራ እስከሚይዝድረስከተያያዝነዉ የፀረ ባርነት ፊልሚያ መስመር ለኣፍታምእንኳቢሆንየሚያዘናጋንአንዳች ገደድ (concern) አይኖረንም። መታሰራችንመገደላችንመሰደዳችንኣልያም ብረት አንስተንለነጻነት ፊልሚያመዉጣታችንለዚህ ክቡር ሰአብኣዊ ተልዕኮ ነዉና ምንጊዜም በኩራት እናስበዋለን።
የጭቆና መንበሩን የተቆጣጠሩ የዘመኑ ወራሪዎችም ሆኑ የቀድሞ ዐሃዳዊ መንግስት ናፋቂዎች በሕዝቦች የጸረ ባርነት ትግል የተናወጠዉን የአገዛዝ መንበራቸዉን ለማጥበቅ አልያም የፈረሰዉን የዐፄ ዙፋናቸዉን መልሶ ለማጽናት በመሻኮት ላይ ስለመሆናቸዉ በዉል እንረዳለን። ለዚህ ዓላማቸዉ ስኬት ደግሞየሕዝባችንን የነጻነት ጥያቄ ለማደናቀፍኣሊያምከተቻላደግሞ  ለማምከን በገሃድም ሆነ በስዉር  ፣  በተናጠልም ሆነ በጋራ ያልተቋረጠጥረት እያደረጉ እንደሆነለመረዳት የየዕለት እንቅስቃሴያቸዉን ከማጤን ያለፈ ሌላ ተዓማኒ መረጃ መፈለግ ኣያሻም።በመሠረቱ የኦሮም ሕዝብ የነጻነት ትግል ማንም ልገዳደረዉ የማይችል ደረጃ ላይ ስለመሆኑ ከነዚህ ኃይሎች ግንዛቤና ዕይታ የተሰወረ ነዉ ቢሎ ማሰብ ኣይቻልም።  ሆኖም ግንመሠረታዊ አፈጣጠራቸዉም ሆነ የሚከተሉት የድንቁሪና መንገድበተጨማሪ አስተዋይነት የራቀዉ  የትምክህት አስተሳሰባቸዉ ዛሬም ራሳቸዉን ከነባራዊ ዕዉነታ ጋር ኣስታርቀዉ፣የሕዝቦችን መብትና ፍላጎት ተረድተዉኢምፓዬርቷን እያናጣት ላለዉ ሕዝባዊ ጥያቄ ዓለም አቃፋዊ ድንጋጌዎችን በተከተላ ስልጡን አካሄድኣዎንታዊ ምላሽ ለመስጠት ኣላስቻላቸዉም።ስለሆነምአሳፋሪና ወራዳ አካሄዳቸዉን የሙጥኝ ብለዉታል።  ይህን በማድራጋቸው ያተረፉት ነገር ቢኖር የሕዝቦችን ሁለንተናዊ ሕይዋት ማቃወስናኢምፓዬሪቷን መዉጫ ወደማይኖረዉ አደገኛ ቀዉስ ማምራት ብቻ ይሆናል።ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ለነጻነት ንቅናቄ ወቅታዊ አቋም

No comments:

Post a Comment