Wednesday, June 12, 2013

የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች-ወያኔ ሕወሃት

une 12, 2013
ይኸነው አንተሁነኝ
ሀገራትም ሆኑ ግለሰቦች እንድን ስራ ለመከወን ይነስም ይብዛ እቅድ ያቅዳሉ። ብዙዎቹ ባለሙያዎች እንደሚስማሙበትም እቅድ አቅምን ያገናዘበና ውጤቱም አርኪ እንዲሆን ለማድረግ ለእቅዳችን የሚያገለግሉ በእጃችን ያሉ ነገሮች ከሌሉት የመለየት መሰረታዊ ፍተሻ መደረግ አለበት። እንዲህ አይነቱ የመለየት ስራ ከአቅማችን ጋር ለመጓዝ ከማገልገሉም በተጨማሪ በእጃችን ያሉና እቅዱን ተፈጻሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የገንዘብ፣ የሰው ሃይል፣ የቋሚና አላቂ እቃዎችን ዝርዝር በትክክል ለማወቅ ያገለግለናል። ከተደጋጋሚ ግዥና ያለአገልግሎት የሚቀመጥ የሰው ሃይል እንዳይኖር ከመጥቀሙም በተጨማሪ አግባብ ያልሆነ የእውቀት መደራረብን ያስወግዳል። ትዲያ ይህ ሁሉ ሃብትን የማወቅ ፍተሻ በራሱ ገንዘብ የሚያሰወጣ ከመሆኑ አንጻር ከፍተሻው የተገኘው ውጤት ለእቅዱ ግብአት ሆኖ ጥቅም ላይ መዋሉ የሚያከራክር መሆን የለበትም። ከዚህ አንጻር የልማት ፊታውራሪ ነኝ የሚለው ወያኔ ሕወሃት ምን አድርጓል ምንስ እየከወነ ነው?
ከዚህ በፊት የነበሩት የሀገራችን አገዛዞች በተለያየ ደረጃ የሀገራችንን ሃብት ተገቢ ባልሆነ መልኩ አባክነዋል። በተለይ በዘር ላይ የተመሰረተው የወያኔ ሕወሃት አገዛዝ ከሀገርና ሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ይልቅ የተወሰኑ ጉጅሌ ስብስቦችን ፍላጎት ለመፈጸምና ለማስደሰት ያለመ በመሆኑ ብዙ ምስቅልቅሎችን ፈጽሟል። እይዘዋለሁ እደርስበታለሁ ብሎ ያሰበውንና እንደሚጨብጠው ገና ያላረጋገጠውን ነገር ለመጨበት ሲል በእጁ የነበረውን ለአገልግሎት የተዘጋጀ እጅግ በጣም ብዙ የሀገር ሃብት በትኗል። የበቆሎ ቂጣ እያረረበት አንድ ቁና የማትሞላ ነጭ ጤፍ በር ላይ በማስጣት ለጎረቤት ነጭ ቴፍ እየበላን ነው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ እንደሚዳዳው አላዋቂ፤ ወያኔ ሕወሃትም የምእራባዊያንን ዓይን ለመጋረድ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ባለፈ ሲምንቶ የተገነቡና ጥራታቸው አስተማማኝ ያልሆኑ ጥቂት ሕንጻዎችን በማቆምና ልማት ላይ ያለ በማስመሰል የሕዝባችንን ችግር የደበቀ ይመስለዋል ከዚያም ሲያልፍ በኔ ያገዛዝ ዘመን አገሩ ሁሉ ድሎት በድሎት ሆኗል ሊለን ይሞክራል ። የአንዲት ሀገር ቁጥር አንድ ሀብት የሆነውን የሰው ሃይል ግንባታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ የትምህርትን ጥራት በመግደል ከመሰረቱ በማጥፋት ላይ ይገኛል።
በራሱ ወያኔያዊ መለኪያ የተሻለ ብሎ የሚያስበውን የውጭ ዜግነት ያላቸውን አስተማሪዎች በከፍተኛ ወርሃዊ ክፍያ በማስገባት ሀገራችን በስንት ድካም ያፈራቻቸውን ብርቅየ ልጆቿን ከነችሎታቸውና ስራ ልምዳቸው ወርውሯል። በዚህም  ለማሻሻል የያዝኩት እቅድ የሚለውን የትምህርት ጥራት ገድሏል። በትምህርት ያልተደገፈች አገር መጨረሻዋ ውድቀት ለመሆኑ ክርክር የሚያነሳ ያለ አይመስለኝም ። በብዙ ኢኮኖሚያዊ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ ኩነት አጥኝ ተቋማት በተደጋጋሚ እየተገለጸ የሚገኘውም ይኸው የሀገራችን ውድቀት መሆኑን ለማስረገጥ ከኛ ከራሳችን በቀር ሌላ ምስክር መጥራት ተገቢ አይመስለኝም። የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የመምህራንና ሌሎች ሰራተኞች መፈናቀልና በዚሁ ሳቢያ እየሞተ ያለውን የትምህርት ጥራት ባቅራቢያችን እያየን ነውና ያለነው።
የፌደራሊዝምን ስርአት በመገንባት ለዓለም ሳይቀር ምሰሌ ሁኛለሁ እያለ ሲያላዝን የከረመው ወያኔ ሕወሃት በዚሁ ሳቢያ በብሔርና ቋንቋ የነበረው መፋጠጥ ወደ ትንንሽ ወረዳዎች ሳይቀር ወርዶ በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ንትርክ አለመግባባትና ያልተቋረጠ ግጭት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል። በተቃራኒው ግን ዓለምን ያስቀና የነበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች መቻቻልና አብሮ የመኖር የሽህ ዓመታት ተሞክራችንን እንደቀላል ነገር በማጣጣል ቀጣይነቱ ላይ አደጋ ደቅኖ ይገኛል።
ወያኔ ሕወሃት የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ለማበረታታት በሚል ሰበብ ባግባቡ ባልተጠናውና ባልተጨበጠው ከፍተኛ የልማት ምኞቱ የተነሳ የራሳችን የነበሩትንና የሰው እግር እረግጧቸው የማያውቁ ሰፋፊ ሃብታም መሬቶችን በግፍ ለባእዳን ከማስረከቡም በተጨማሪ ከዚህ በሗላ መቼም ልንተካቸው የማንችላቸውን እድሜ ጠገብ አገር በቀል የደን ሀብት በዚሁ ልማት ሰበብ እንዲጨፈጨፍ አድርጓል። በውስጡ ይገኙ የነበሩና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን ሊስቡ ይችሉ የነበሩ ብርቅየ የሀገራችን የዱር እንሰሳትና አእዋፍ የትም እንዲበተኑና እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።
ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስታውሰው ላልተጨበጠ የሰላም ድርድር የሀገርን ሉአላዊነትና ዘላቂ ጥቅም ባላስጠበቀ ሁኔታና የሕዝብን ፍላጎትና ሰላም ባላገናዘበ መልኩ ድንበርን ቆርሶ ለጎረቤት በመስጠት ለዓለም ሀገራት ፋና ወጊ የሆነው ወያኔ ሕወሃት መሆኑ አይዘነጋም። በዚህ የተነሳም ምንም እንኳ ወላጆቻችን የሞቱለት ድንበራችን ተቆርሶ ቢሰጥም ለሀገራችን የተጠበቀው ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ግን እስካሁንም አልተገኘም።
በጥቅሉ የአንዲት ሀገር እድገትና ብልጽግና መሰረቱ የራሷ ሕዝብ የሚያደርገው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ  ቢሆንም ወያኔ ሕወሃት ግን ከውጭ የሚመጡ መዋእለ ነዋይ አፍሳሾች የተሻለ ሀገራችንን ይገነባሉ ያሻሽላሉ ብሎ በማሰቡና ለሀገራችን ባለሃብቶች ትብብርን በመንፈጉ፤ ሕብረተሰባችን ለልማት ያለው ተነሳሽነት እየሞተ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም “ለውጭ ባለሃብቶች ተቀጥረን በመስራት እንጅ እኛ በራሳችን ልማት ልናመጣ አንችልም” የሚለውን ደካማና መጥፎ አመለካከት በሕዝባችን የሚያሰርጽና ሁለንተናዊ ውድቀትን የሚያመጣ አካሂያድን መርጧል- ወያኔ ሕወሃት። ይሁን እንጅ ከውጭው መዋዕለ ንዋይ ፍሰት የተገኘ ጠብ ያለ ነገር የለም በተቃራኒው ግን ስራ መስራት የሚችለው ሕዝባችን ከዚህ የኢኮኖሚ ዘርፍ እየተገፋ እየወጣ ይገኛል።
በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ አስታራቂና ሰላም ፈጣሪ መስሎ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ሕወሃት በሕዝባችን ላይ ግን ይህ ቀረሽ የማይባል አፈናና ጭቆናን በማውረድ ተሸብሮ በማሸበር ሕዝባችንን ሰላም በማሳጣን ላይ ነው።
በእርግጥ አልሆነም እንጅ ወያኔ ሕወሃት የሚለው ልማት በሀገራችን ተፈጥሮ ቢሆን እንኳ በሕዝባችን ተከውኖና የሀብት ክፍፍሉም ተመጣትኖ ሕዝባችንን ከርሃብ እስካላዳነ ድረስ ምን ጥቅም አለው? እናቱ ወይም አባቱ እህቱ ወይም ወንድሙ በችጋር የሚቆሉበት ባለጸጋ በጓደኞቹ ፊት ምን ክብር አለው? በዓለም ፊት እየደረሰብን ላለው የርሃብ የጉስቁልናና የስደት ተደጋጋሚ ችግር ዋና ምክንያት የሆነው ወያኔ ሕወሃት እንኳን ያላመጣውን ልማት መለፍለፍ ይቅርና ቢያመጣ እንኳ በዓለም ፊት ምን ክብር ሊያገኝ ይችላል? የኑሮ ውድነትን ርሃብንና ስደትን የመሳሰሉ ዋና ዋናዎቹን የሕዝባችንን ችግሮች አስወግዶ እስካልታየ ድረስ።
አዲስ ሚስትና ንጉስ አፍርሶ ይሰራል እንደሚባለው ነው እንጅ የዘረኝነት ጥማቱን ከማርካት በቀር ለሕዝባችንስ በችግር ላይ ችግር እንጅ ሌላ አልታየም።  የራስን ብርቱና ጠንካራ ሃይል በመበተን በሌሎች ላይ መተማመንስ እስከ መቼ ያዛልቃል? በጁ ያለውን የራሱን በትኖ በሌሎች የሚመጻደቅ እንደ ወያኔ ሕወሃት ያለው የህዝብን ጥቅምና ፍላጎት የማያስጠብቅ ጎጠኛ ገዥ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ እንጅ የውድቀት ጉዞውን እያፋጠነ ለመሆኑ ከራሱ ድርጊት በቀር ሌላ ማረጋገጫ የለም።

2 comments:

  1. this is one of the most surprising paradoxes I observe among few Ethiopians; They claim the Amharas and Tigres are not EThiopians because they are Abyssinians. Then, the Oromos are not Ethiopians...huh
    Who is Ethiopian then?
    I would accept if one says that the Semitic speakers of Ethiopia are not Ethiopian; they seem to speak a non-AFrican (kind of mix) language at least, (even if the Semitic roots of most of Ethiopian languages is very exaggerated, specially for south and Transversal groups such as Amharic, Hareri and Gurage; there are a dozen of reasons to take these language groups as Cushitic. I am a linguist myself).

    But, claiming Oromo people as non-Ethiopian is the acme of ignorance one can live with. Nobody in the world is more Ethiopian than the Oromo people, if one knows a little history of the black people (Kush).
    ---
    Great article.
    I am not interested in the current Ethiopian politics. But, the denial of history enrages me.

    ReplyDelete
  2. Just shut up!"Doma" for the first time,i am using this word

    ReplyDelete