Monday, October 7, 2013

በጣሊያኑ የባህር አደጋ የሞቱት የ153 የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን ስም ዝርዝር

በጣሊያኑ የባህር አደጋ የሞቱት የ153 የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን ስም ዝርዝር


italy
ሰሞኑን ከሊቢያ ተነስተው በጣሊያን ባህር አቅራቢያ ባህር ውስጥ ጠልቀው ከሞቱት ወገኖች ውስጥ በተለያዩ ሚዲያዎች የኤርትራ ስደተኞች ብቻ እንደሞቱ እየተዘገበ ነው። ዘ-ሐበሻ ግን የኤርትራ ስደተኞች መባሉን አታምንብተም። የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ በሊቢያ ስደት ውስጥ ያሳለፈ በመሆኑና ወደጣሊያንም በባህር ለመሻገር ሞክሮ በእስር ምክንያት ሕይወቱ በመትረፉ ዛሬ የኤርትራ ስደተኞች ብቻ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተደርጎ መወራቱን አይቀበለውም። በሊቢያ ቤንጋዚ፣ ትሪፖሊ፣ ኩፍራ፣ ኢጅዳቢያና ሌሎችም እስር ቤቶች በርካታ ከምስራቅ አፍሪካ ወደ ጣሊያን ለመሰደድ ሄደው የታሰሩ ሰዎች ከዘ-ሐበሻ አዘጋጅ ጋር የታሰሩ ነበሩ። እነዚህ ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያኑ እስር ቤት ሲገቡ ዜግነታቸውን ‘ኤርትራዊ እንደሆኑ እንዲናገሩ” አሻጋሪዎች ይነግሯቸዋል። ምክንያታቸውም የሊቢያ መንግስት እስር ቤት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለን ወደ አዲስ አበባ ስለሚሸኘው፤ ኤርትራዊ ነኝ የሚል ግን ወደ አስመራ ስለማይላክ ሁሉም ኢትዮጵያዊም ኤርትራዊም “ኤርትራዊ ነኝ” ብሎ ነው የሚገልጸው። አሁንም የሆነው ያ ነው። ኤርትራዊያን ናቸው ከተባሉት ውስጥ አብዛኛው ኢትዮጵያውያንም ጭምር ናቸው በሚል ዘ-ሐበሻ ታምናለች።
የሞቱትን ነብሳቸውን ይማረው፡ የሟቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው፡
Via: Zehabesha

No comments:

Post a Comment