Sunday, November 17, 2013

ህዳር 9 የሚከበረውን የፀረ-ባርነት አመፅ ቀን አስመልክቶ ከኦሮሞ የወጣቶችን ነጻነት (ቄሮ) የተሰጠ መግለጫ

Qeerroo

ህዳር 9 የሚከበረውን የፀረ-ባርነት አመፅ ቀን አስመልክቶ

ከኦሮሞ የወጣቶችን ነጻነት (ቄሮ) የተሰጠ መግለጫ 

ባለፈው አንድ አመት (ከህዳር 2012 እስከ ህዳር 2013) ውስጥ የታሰሩ፣ የተገደሉና የደረሱበት ያልታወቀ የኦሮሞ ልጆችን በተመለከተ፤

የኦሮሞ ህዝብ ለወያኔ አገዛዝ አንድም ቀን ፍቃደኛ ሆኖ አያውቅም፡፡ በመሆኑም ባለፉት 21 ዓመታት ይህን ጨቋኝ ስረዓት በመቃወም ብዙ መስዋትነትን ከፍሏል፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ የመብት ጥያቄ የሚያነሱትን በየጊዜው አድኖ ማሰርና ማፈን የወያኔ መንግስት የአስተዳደር ስረዓት ባሕል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ከህዳር 9/2012 እስከ ህዳር 9 2013 የፀረ-ባርነት አመፅ እያካሄዳችሁ ነው ተብለው በርካታ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎች እስር ቤት ውስጥ የታፈኑ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ የተገደሉና የደረሱበት ያልታወቁ ናቸው፡፡ ባጠቃላይ በዚህ አንድ አመት ውስጥ በርካታ የፀረ-ባርነት አመፆች በመላው አገሪቷ ተካሂዷል፡፡ ወያኔም እስራትና ግድያ ሲፈፅም ነበር፡፡ በዚህ አመት ውስጥ ለኦሮሞ ነጻነት ሲታገሉ የታሰሩ፣ የተገደሉና የት እንደደረሱ ያልታወቁትን ለማስታወስና በአለም ላይ የሚገኘው ብሔረሰባችን የታጋዮቻችንን መብት ለማስከበር በሁሉም ቦታ እንዲፋለም የኦሮሞ የወጣቶች ነጻነት ንቅናቄ የታሰሩትን፣ የተገደሉትንና የት እንደደረሱ የማይታወቁትን መችና የት እንደታሰሩ ችምር መዝግቦ እንደሚቀጥለው አቅርቧል፡፡
በህዳር 11 2012 ምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ ውስጥ የሀገር ባለቤትነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ጠይቃችኋል ተብለው ከስራ የተባረሩ የኦሮሞ ልጆች፡-
1. አቶ ግርማ አራርሳ – የኤጄሬ ወረዳ ረዳት የእንሰሳት ሀኪም
2. አቶ አበበ ግዲራ – የኤጄሬ ወረዳ ረዳት የእንሰሳት ሀኪም
3. አቶ ደቀባ ተፈራ – ረዳት የእንሰሳት ሃኪም
በኢሉባቦር ዞን ጮራ ወረዳ የተጠየቁትን የመብት ጥያቄዎች ከኦነግ ጋር በመሆን እያቀናጀ ነው ተብሎ መምህር አበበ ተካ ህዳር 14/2012 እ.አ.አ ወያኔዎች አፍነውት እስር ቤት ወስደውታል፡፡
ህዳር 15/2012 እ.አ.አ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተከታታይ ሲነሱ ከነበሩት የመብት ጥያቄዎች ጋር ተያይዞ መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለወያኔ መንግስት ጥላቻ አላችሁ ተብለው ከዩኒቨርሲቲ የተባረሩ የኦሮሞ ልጆች፣-   Read More:- ህዳር 9 የሚከበረውን የፀረ-ባርነት አመፅ ቀን አስመልክቶ

No comments:

Post a Comment