Saturday, December 21, 2013

ገደብ ያጣው ግፍና የጭቆና መረብ በኦሮሞ ትውልድ ላይ

By Getinet Dinkayehu
የወያኔ እነቅስቃሴ በኦሮሞ ህዝብና በኦሮሞ ድርጅታዊ እነቅስቃሴ ላይ ያላቛረጠ ጭቆናና የመብት ረገጣ በማድረግ የተለያዩ ኢ-ዲሞክራሳዊ የመብት ጥሰቶችን እየፈፀመ ይገኛል:: ለዚህም ስትራተጂዎችን በመንደፍና የነደፈውን በመተግበር ዛሬ አለም የሰዉ ልጆችን መብት ከመጠበቅ አልፎ የእንስሳትን መብት እየጠበቀ ባላበት ዘመን ላይ የኦሮሞ ልጆችን መብት በማሳጣት ከአለም ሚዲያዎች በመሰወር እንዲሁም በግልጽ እየረገጠ ይሄው ድፍን 22 አመት አለፈው። የአለም መንግስታት ወያኔ በላዩ በሽፋን የያዘውን ዲሞክራሲ የሚል የውሰጥ መርዝና ገዳይ ስራውን በተለያየ መንገድ ቢገንዘቡትም የኦሮሞ ህዝብ ችግር ግን ሰሚ ያጣ ይመሰላል። የአንድ ብሄር ዝርያዎች ብቻ በስልጣን ላይ መቀመጥና መግዛት የለሎች ብሄሮች በህይወትና በሞት መሃል ተገዝቶ መኖር የኦሮሞ ህዝቦች ደግሞ እያጣጣሩ እንኴን እንዳይኖሩ በሚደረግበትና የወያኔ የእስር ቤት ቋንቌ ኦሮምኛ በሆነበት በዚህ ወቅት ዲሞክራሳዊ አስትዳድር አለን ብለው በዉሸት ህዝብንና አለምን ለማታለል መሞከር ገዢው ወያኔ በፍፁም ዲሞክራሲን በስም እንጂ በተግባር የማያውቅ መሆኑን ለተመለከተው ሰው ሁሉ ግልፅ ነው።
በየትኛው ዲሞክራሲ ያለበት ሀገር ላይ አንድ መንግስት ለ22 ተከታታይ ዓመታት በግፍ እንደሚገዛም እኔ አላውቅም ።
ባለፉት ረጅም ዘመናት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ስልጣን ነው እያሉ የኦሮሞ ልጆችን በግፍ እንደ በግ ስያርዱ፣ስያስሩ፣ሲገርፉና በቆሻሻ እንደተነካ እንጨት ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ማንነቱን ስያንቌሽሹ በነበሩት አፄዎች ስንገዛ ነበር ። ያ ሁሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች ላይ የደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል ጭራሽ እንደ ፅድቅና ቅድስና ተቆጥሮላቸው ሰሞኑን በቤተ ክርስታናቸው ውስጥ ዛሬም የዱሮውን ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ባሉት ክፋትን በተሞሉ ልጆቻቸው 100ኛ አመታቸው ሲዘከርላቸው ስመለከትና የብዙ ሺ የኦሮሞ ልጆችን ደም ስያፈስ የነበረው የወያኔ ክፉ መሪ ዛሬም እንደ ትልቅ ጀብዱና ታላቅ መሪ ታይቶ በዚች ውሽት በሞላባት አለም ላይ ሲወደስ ሳይ የአለም ክፉነት ገደብ እንደለለው ያሳየኛል።ይሄንን ሁሉ ግፍ ከኦሮሞ ህዝብ የዋህነት ጋር ሳነፃፅረው በጣም ያሳዝናል። የዋህነታችን አልጠቀመንም ጐድቶናል፣ በድሎናል ።
የአሁኑ የወያኔ የዉስጥ ገዳይ የአገዛዝ ስልት ደግሞ የሰሚ ያለህ ብሎ የሚያስጮህ፣የሚያስመርር ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅትም በሃገር ዉስጥ በኦሮሞ ወጣቶች የሚደረግ የነፃነት ትግል እየጠነከረ በሚሄድበት ግዜ ሁሉ ወያኔ መነሻው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ነው በሚል በተለመደው የሂሳብ ስሌቱ የኦሮሞ ልጆችን እየገደለና እያፈሰ እስር ቤት ከማጎር አልፎ የኦሮሞን ህዝብ የነፃነት ጉዞ ለማዳከም  የተለያዩ መርዛማ ዘዴዎችን በመጠቀም የኦሮሞ ህዝብንና የነፃነት ትግልን ለመለያየት ብሎ ለሰው ልጆች የማየገባን የጭካኔ ግፍ እየተገበረ ነው ።
የዛሬውን አያድርገዉና የኦነግ ድርጅት ወያኔን የትግል ስልትና አካሄድ በማስተማር እንዲሁም ደርግን በመጣል ረገድ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ ቢሆንም ከትግል ይዞት የገባውን አጀንዳ እንዳይፈጽም መጠነ ሰፊ ተግዳሮቶች በወያኔ መንግስት የገጠመው ከመሆኑም ባሻገር የኦሮሞን ህዝብ ለማታለል በወያኔ ሳምባ በሚተነፍስና የወያኔን ጭምብል ባጠለቀው የኦህዴድ ድርጅት የኦሮሞን ትውልድ በእጅ አዙር ለመግዛት ስልታዊ የሆነ የአገዛዝ መረቡን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ዘርግቶ በደሎቹን ለመሸፈን  የኦሮሞን ህዝብ የሚያስተዳድረው ኦሮሞ ነው በማለት ይስበክ እንጂ ኦሮሞን እያስተዳደረ ያለው ኦሮሞ እንዳይደለ እንዃን ህዝቡ የአለም ህዝብ ያውቀዋል :: በቅርቡ ደግሞ ድምበር በመሻገር ከጎሮበት ሃገራት ጋር ጠላቴ ነው ሲል ከነበረው ከኤርትራ መንግስት ጭምር ድርድር ለማረግ ፕሮፖጋንዳ መንዛት መጀመሩ ጉዞው ወደት እንደ ሆነ ለመረዳት አያስቸግረንም።
ኤረ ለመሆኑ የኦሮሞ እስትዳደር ለኦሮሞ ያሰፈልጋል ብሎ ወያኔ ካመነበት ለምንድን ነው ኦነግን በጥይት የሚያሳድደው ?
በርግጥ ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ድርጅት ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ የማንነት መገለጫ መሆኑን ወያኔ ጠንቅቆ ያውቀዋል። ለዝህም ነው በጥይት ኦነግን ማሳደድ የኦሮሞ ህዝብን ማንነት አጥፍቶ ያለገደብ በጨለማ ለመምራት ብቸኛው ምቹ መንገድ እንደ ሆነ በማሰብ ያለ እረፍት እየሰራበት ያለው።
ለዚህም የሃገሩን ሰርዶ በሃገሩ በሬ እንደሚባለዉ ተረት ወያኔ በስሩ ባቋቋመዉ በራሱ ሳምባ በሚተነፍስ የኦህዴድ ድርጅትን በመጠቀም የኦሮሞ ህዝብን የማንነት ስሜት ለማጥፋትና ሀገሩን ለመበዝበዝ ህዝቡን በመከፋፈል፣በማጨፋጨፍ፣የኦሮሞን የነጻነት ትግል እንቅስቃሴዎች ለማፈንና ወደ ኋላ ለማስቀረት ከሊስትሮ ጀምሮ እስከ ላይ ድረስ በጥቅም ፈረስ ላይ ሆነው በሚጋልቡት ደህንነቶችንና አጨብጫቢዎችን በማሰማራት ከፍተኛ ጭቆናና በደል እያደረሰ እንዲቀጥል ምቹ ከለላ የሆነለት ይመስላል:: ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እንደ ኦህዴድ ባለው የውሸትና ሆድ አደር ስብስብ ተመልሿል ብሎ ወያኔ በመስበክ የኦሮሞን ህዝብ በሙሉ ያታለለ መስሎታል። እዚህ ጋ ሳልናገር የማላልፈው ነገር ቢኖር ግን የኦሮሞ ህዝብ ጥያቀ በቋንቋው መናገር ብቻ አይደለም ። በዚህ ብቻ 40 ሚሊዮን ህዝን ለማታለል መሞከር ሞኝነት ነው። ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ እስኪመለስና ኦሮሞ በራሱ ሀገር ላይ የባለበትነት መበቱን እስኪጎናፀፍ ድረስ ወያኔ ለግዜው እንዲሁ ይለፋል እንጂ የኦሮሞን የነፃነት ትግል ለማዳከምም ሆነ ለማጥፋት መላውን የኦሮሞን ህዝብ ካልጨረሰ በቀር መቼም እንደማይሳካለት ነው። አንድ ቀን እሮሞ ነፃ መውጣቱ ስለማይቀር ነፃነቱን ያገኜ ቀን ግን ላደረሱት በደለ ወንጀለኞቹን ከጥቅም አጨብጫቢዎቻቸው ጭምር በፍርድ እንደሚፋረዳቸው አንዳች ጥርጥር የለዉም::
የወያኔ መንግስት በየወቅቱ እንደ እስስት እራሱን እየቀያየረ የሚኖር ከመሆኑም በተጨማሪ ጠዋት የተናገረዉን ማታ መድገም በማይችሉ የውሸት ቛጥ በሆኑ ካድረዎች የኦሮሞን ህዝብ እየዘረፈ ለመግዛት ፣ በመግደል፣ በማሰርና የኑሮ ዋስትናን በማሳጣት ከአገር እንዲሰደድ ለማረግ ስልቱን በመቀያየር እየሰራ መሆኑን መገንዘብ ያለብን ይመስለኛል።
የወያኔ እስስታዊ ባህሪና የውስጥ ገዳይ ስልቶችን በኦሮሞ ላይ የሚተገብርባቸው መነገዶች
በግልፅ የውሸት ሽፋን ያለውን አፋኝ ህግ በማውጣት
የሃገሪቷን 6% የማይሞላው የህወሓት የማፍያ ቡድን አብዛኛውን ዋና ዋና የአገሪቷን ሥልጣኖች በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ውስጥ በማስገባት የፖለቲካ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎችን ጭምር በሞኖፖሊ በመቆጣጠር መሪውን ይዞ ወደፈለገበት እያሽከረከከረ ከመገኘቱ ባሻገር የራሱን የስልጣን እድሜ ለማራዘም ሲል ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ላይ ባነጣጠረ መልኩ አፉን ለማፈን ህጎችን እንደፈለገ በማውጣትና እንደፈለገ በመተግበር ላይ ነው ።
ከእነዚህም መካከል በትልቁ በአለም ሚዲያዎች የሚታወቀውን ወያኔ በግልፅ በህገመንግስቱ ላይ በቅርብ ያወጣዉ የአሸባሪነት ህግን የሚመለከት ይሆናል። አሁንም ይህን ሃሳብ ሳነሳ የሰሚ ያለህ ብሎ የሚያስጮህ ነዉ።
በአለም ላይ የፀረ አሸባሪነት ህግ የወጣው በዋናነት ንፁሃን (innocent) ህዝቦችን ከሽብር ለመከላከል ሲሆን የፀረ አሸባሪነት ህግ በወያኔ የወጣበት ዋናው ምክንያት ግን ንፁሀን(innocent) የሆኑትን የኦሮሞ ልጆችንና ለሎችንም ለማሸበር ታስቦ የወጣ መሆኑ ግልፅ ነው።በለላ አነጋገር አለም የፀረ አሸባሪነትን ህግ የምትጠቀመው ንፁሃን ህዝቦች እንዳይሸበሩ ለመከላከል ሲሆን ወያኔ ግን ንጹሃን ህዝቦችን እራሱ እያሸበረበት ነው።
የኦሮሞ ህዝብ በየትኛዉ ስራዉ ነው በአለም ህዝብ የሚታወቀዉ ? በአሸባሪነት? ለመብትና ለነፃነት መታገል፤በሀገራችን ላይ የባለበትነት መብት ይሰጠን ማለት፤የኦሮሞ ህዝብ መተዳደር ያለበት በኦሮሞ ነው ማለት፤ሀብትና ንብረታችንን አትስረቁን አትበዝብዙን ማለት አሸባሪነት የሚያስብል ከሆነ እንግያውስ አለም ሁሉ አሸባሪ ናት ማለት ነው:: ለነነገሩ አለም ባታዳላ ኖሮ የኦሮሞ ህዝብ እስከዛሬ ድረስ በባርነት ስር ባልኖረና ነበር:: የወያኔ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ ለማሰርና ለመግደል እንዲሁም ከሃገር ለማባረር በቀን እንዲህ አይነት ህግ አዉጥቶ ኢየሰራበት መገኘቱን ስመለከት ለካ አለም አባት የላትም እላለው::በርግጥም አባት የላትም።
ትንሽ አሻሮ ይዞ ወደ ቆሎ ጠጋ የሚባለዉን የተረት አባባል በመያዝ ወያኔ በአለም ላይ የወጣዉን የአሸባሪነት ህግ በተሳሳተ መንገድ በመጠቀም አንድን ብሄር(ኦሮሞን) ለማጥፋት ሲጠቀም የአለም መንግስታትና የሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ዝምታን መምረጥ በኦሮሞ ላይ የሚደርሰውን በደልና ጭቆና የከፋ እያደረገ ይገኛል:: የአንድ አምባገነን መንግስት የዘር ማጥፋት ህግ በማዉጣት የሰዉን ልጅ ያለገደብ መጨፍጨፍ መች ነግቶ በማን ይጠየቅ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ከምያደርሱት በደል በተጨማሪ የእነሱን የግፍ አገዛዝ በመሸሽ ወደ ጎሮበት ሀገራት ሄደው በፖለቲካ ጥገኝነት በUNHCR ተመዝግበው የሚኖሩትን የኦሮሞ ልጆች እንኳ በሰላም እንዳይኖሩ ባሉበት በማሳደድ የፀረ አሸባሪነት ህግን በሽፋን በመጠቀም ከጎሮበት መንግስታት ጋር ስምምነት ፈጥረው እጅ እግር አስረው በመመለስ የእድሜ ልክና የሞት ቅጣት ቀማሽ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑ የዚህን ህግ አስከፊነትን ያመለክታል።እንደ ምሳሌነት ብናነሳ በቅርቡ ወጣት እንጅነሮች ተስፋሁን ጨመዳና መስፍን አበበ ከኬኒያ የተያዘበት ዜደና በወያኔ እስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸው አሰቃቂ ግድያ መላውን የኦሮሞ ህዝብ ያስለቀሰ ጉዳይ ነው።በአሁኑ ግዜም በዚህ የወያኔ ፀረ ሽብር ህግ ምክንያት በጎሮበት ሀገራት በፖለቲካ ጥገኝነት የሚኖሩ የኦሮሞ ልጆች ተሰሚነት አያጡ በስጋት ውስጥ እየኖሩ መሆኑን በተደጋጋሚ እየሰማን ነው።
የሽፍተኝነት ባህሪን በመላበስና በመግደል
የወያኔ መንግስት ፀረ ህዝብ ፤ፀረ ዲሞክራሲ ፤ፀረ ኦሮሞ ነው ብየ ብገልጽ የአደባባይ ሃቅ ነው። ይህንን ለማለት የቻልኩበት ምከንያት ወያኔ ደርግን ለመጣል የተነሳሳውና ወደ ጫካ ገብቶ በሽፍተኝነት ጀምሮ ለድል የበቃ መንግስት ሲሆን ደርግ በአደባባይ ነጭ ሽብር ቀይ ሽብር እያለ የንፁሀንን ደም ስያፈስ ወያኔ በሚድያዎቹ ሲኮንንና ሲከስ ስለነበረ እራሱን ከደርግ ሥርዓት የተሻለ አድርጎ የሚቀርብ ይመስል ነበር:: ነገር ግን ዛሬ የደርግ ጭፍጨፋ መልኩን ቀየረ እንጅ በሀገሪቱ ላይ በወያኔ እየተደረገ ያለው በደል ከደርግ የባሰ እንጂ የሚያንስ አይደለም ።
በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የኦነግ ሰራዊቶችን በሰላማዊ መንገድ በድርድር በነበሩበት ወቅት ትጥቅ አስፈትቶ በካምፕ ዉስጥ በማስገባት ትጥቅ የፈታን ህዝብ በታንክና በከባድ መሳሪያ መጨፍጨፉ አሰቃቂ የአደባባይ ግድያውን የምያመለክት ሲሆን በተጨማሪም በካድረዎቹና በደህንነቶቹ ጥይት በየግዘው በአደባባይ የሚገደሉትን የኦሮሞ ልጆች ደግሞ ቤት ይቁጠራቸ። አሁን አሁን ደግሞ ወያኔ የሰዉን ልጆች ለማጥፋት የሚጠቀመው መጠነ ሰፊ ስልቶች ሲኖሩት እያራመድኩ ያለሁት ዲሞክራሲ ነው ብሎ ለመስበክ እንዲመቸው በተወሰነ መልኩ በአደባባይ የሰዉን ልጆች ከማጥፋት ሲልቱን በመቀየር የሽፍተኝነት ባህሪውን አሁንም በንፁሃን የኦሮሞ ልጀች ላይ እየተገበረ ይገኛል::
ከነዚህ የወያኔ የማፍያ ስልቶች መሃከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያክል የሰዎችን መውጣትና መግባት በመጠበቅ በመኪና ገጭቶ መግደል እንደዚሁም ሽፍታ የገደለ ለማስመሰል የታጠቁ ሰራዊቶቹን ጫካ ዉስጥ በማስቀመጥ የሚፈልጉትን ሰው በማስገደል እንደዝሁም አንዱን ለማሰር ለላዉን ለመግደል በሚፈልጉበት ጊዜ ደግሞ ስውር ስራቸዉን ለመፈጸም ለአንዱ ጥይት በመስጠት ለላውን አስገድለው ወያኔ ከዜሩ ውጪ ለማንም ዘመድ መሆን ስለማይችል ገዳዩንም ወንጀለኛ ነህ በማለት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የሚለውን አባባል በስዉር ስራቸው ሲተገብሩት እናያለን። የእርሱ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ሰዎችን ድርጅት በመፈለግ በካድረዎቹ በተቀናበረ የፈንጂና የቦምብ ፍንዳታዎች ንፁሃን ዘጎች ባሉበት ቦታ እያፈነዳ በአንድ በኩል እርሱን የሚቃወሙ ሰዎችን ንብረት ሲያወድም በለላ በኩል የንፁሃንን ደም ማፍሰሱ ለማንም ግልፅ ነው። እንደማስተባበያ ሲወስድ ግን የኦሮሞን ህዝብ እና የኦነግን ድርጅት አላማ በለሎች ዘንድ ለማጥቆርና ጠላትነትን ለማብዛት እንዲሁም የሚፈልገዉን የኦሮሞ ልጆች ለማሰር ኦነግ ነው ያፈናዳው ብሎ ተሳስቶ እንኴ እውነት ተናግሮ በማያውቀው ሚዲያው(ETV) በኩል ታፔላ ለጥፎ መለፈፉና የዉሸት ፍርድ ሲሰጥ ማየቱ የወኔን አሸባሪኔትና የሽፍተኝነት ባህሪውን ይገልፃል። ያለምንም ወንጀል ታፍነው በመያዝ በተሰቦቻቸው እንኴ የት እንደደረሱ ሳያውቁ ታስረው ለዘመናት የሚሰቃዩትንና በየ እስር ቤቱ በተለያየ አይነት ዘዴ በስውር የሚገደሉትን የኦሮሞ ልጀች ደግሞ እስር ቤቱ ይቁጠራቸው::
የኢኰኖሚ አውታሮችን ጠቅልሎ በመያዝ የኑሮ ዋስትናን ማሳጣት
ከነዚህ ዋና ዋና የግድያ ስልቶች በተጨማሪ ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጠላትነት በመፍጠር ህዝቡን ከህዝብ ጋር ማጋጨትና የትግል አቅም ለማሳጣት ህዝቡን መለያየት የኢኮኖሚ እድገትና የእውቀት እድገት እንዳይኖር ማድረግ ሃብትና ስልጣን እዉቀትና እዉቅና በገዢ ፓርቲ ዘሮች ቢቻ እንዲሆን ማድረግ ከዋነኛዎቹ የወያኔ ስራዎች ጥቂቶች ናቸው::
እንደ ምሳሌነትም በሃገር ዉስጥ የሚኖር የትኛውም የኦሮሞ ተወላጅ እና የኦሮሞ ስም ያላቸዉ ሰዎችን ጨምሮ በነ አፄዎቹ ግዘ የኦሮሞ ስም ማዉጣት እንደ ሃጥያት የሚቆጠርና በአከባቢዉ ገዢዎች ተጠርተዉ ወላጆች የልጆቻቸዉን ስም እንዲለውጡ ከመነገር አልፎ የሚያወጣዉ ስም ምን አይነት ስም መሆን እንዳለበት ከማስጠንቀቅያ ጭምር የሚነገረዉ እንደነበረ የቅርብ ግዘ ትዝታ ቢሆንም ዛሬ ደግሞ የወያኔ መንግስት እንደነ አፄዎቹ የወጣዉን ስም እንዲቀይር ባያደርግም እንኳ የኦሮሞን ህዝብ የሚለይበት መለያ አድርጎ ሲጠቀምበትና እንኴን ኦሮሞ ሆኖ የኦሮሞ ስም ያለው ማንኛዉም ግለሰብ በየትኛውም መስራ ቤትና የስራ መስክ ተሰማርቶ እንዳይሰራ የመስራት መብቱን ተነፍጎ በካድረዎቹ እየተሰደበና ሞራል በሚነካ ኪፉ ንግግር ብቃት እያለው ብቃት እንደለለው በመቁጠር የኑሮ ዋስትናን ማሳጣትና ኢኮኖሚውን በስሩ ጠቅልሎ በመያዝ የትኛውም የኦሮሞ ህዝብ ለትግልና ለነጻነት መክፈል የሚገባዉን እንዲከፍል የሚገፋፋውና የምያነሳሳው የወያኔ ክፉ ስራ መሆኑ ሊጠቀስ ይችላል::
የኢኮኖሚው በአንድ ገዢ መንግስት ዘር መጠቅለሉ በሃገር ዉስጥና ከሃገር ውጪ ያሉ ካምፓኒዎች በሙሉ የመላው የትግሬ ህዝብ ባይሆንም በጥቂቶች በስልጣን ላይ በተፈናጠጡ ትግሬዎች የሚንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው ግልፅ ነው:: በዝርዝር ማቅረብ ብያስፈልግ ከ500 በላይ ካምፓኒዎች የነሱ እንደሆነ በተለያየ ግዜ በጋዘጣዎች ላይ የወጣዉን መመልክት ይቻላል ። በዱባይና በለሎችም የአረብ ሃገሮች የተለያዩ ትልልቅ ድርጅቶችን ከፍተው እየሰሩና በለላው ህብረተሰብ ላይ ጫና እየፈጠሩ ስለመሆናቸው ደግሞ የአደባባይ እውነት ነው:: የውጪን ንግድንም በሚመለከት ደግሞ የፓርቲው የዘር መንግስት ዝርያ ካልሆነ በስተቀር እቃው ከሚሸጥበት ዋጋ በላይ ቀረጥ በመጫን የገዢው ፓርቲ ዘር ከሆነ ግን ቀረጥ ነፃ እቃዎችን በማስገባት የለሎችን የኑሮ ዋስትና እያሳጣና እያስመረረ እንዲሰደድ እያደረገ ይገኛል::
የእነሱ ሹማምንት በሃብት ላይ ሃብት፤ በድሎት ላይ ድሎት፣ በእውቀት ላይ እውቀትን ሲጨምሩ፣ የአብዛኛው ኦሮሞ ህዝብ እጣ ፈንታ ግን መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መንገላታት፣ መታሰር፣ መደብደብና መገደል ነው።የወያኔ ዘሮች የኦሮሞን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ ሲጸድቁና የተንደላቀቀ ኑሮ ሲኖሩ ለላውም ህብረተሰብ በተጨማሪ በኦሮሞ መሬት ላይ የትልልቅ ፎቆችና ካምፓኒዎች ባለበት በመሆን ሲበዘብዙና ሲዘርፉ መከላከያ ያጣው የኦሮሞ አርሶ አደርና የኦሮሞ ወጣት ግን በሀገሩና በየ ስደት በረሃው ላይ በረሀብ ጠኔ እየተሰቃየና እየረገፈ ይገኛል።
እንደ ኦሮሞነት ሳስብ ብዙ ግፎችና በደሎች ተፈፅሞብናል እየተፈጸመብን ነው ። ከዚህ በላይ ግን ምን እስከምንሆን እንደምንጠብቅ አላውቅምም ወይም አልገባኝም።
ጭራሽ አሁን ደግሞ ገና የኦሮሞ ስም ሲነሳ ሁሉም በአንድነት እሳት ጎርሰው እሳት ለበሰው ይነሱብን ጀምረዋል ። ይህ ሁሉ የምያመለከተው ከወደ ሰሜን የሚነሳ ሁሉ የጭካኔ፣የገዳይነት፣የዘረፋና የለላውን ማንነት የማንቋሸሽ መንፈስ እንጂ የቅንነትና የርህራሄ መንፈስ የለለው መሆኑን ነው።ከእንግዲህ ግን በበኩሌ እንዲህ አይነት ጭካኔ በሁሉም አቅጣጫ በከበበንና ሊያጠፋን አፉን በከፈተብን ዘመን ውስጥ ሆነን የዋህነታችን ከኛ ጋር መቀጠል የለበትም ባይ ነኝ ።ምክንያቱም እንደዚህ አይነት በክፋትና በጭካኔ ከተሞሉና ትንሽ ይሉኝታ እንኳ ከለላቸው የገዢ መደቦች ጋር ኦሮሞ መኖር የሚችልበት ደረጃ ላይ አይደለም።ይቀጥላል
ድል ለተጨቋኙ የኦሮሞ ህዝብ!
getinetdinkayeh

No comments:

Post a Comment