Thursday, December 25, 2014

በተለይ ለወደፊቱ ሀገር ተረካቢ ወጣት ሲኦል መሆኑ ቅጥሏል

ወያኔ በሀገራችን የዘረጋው ማህበራዊ ፖለቲካዊና የኢኮኖሚ ስርአት ለጠቅላላ ህዝባችን፣ በተለይ ለወደፊቱ ሀገር ተረካቢ ወጣት ሲኦል መሆኑ ቅጥሏል። በሀገሬ ውስጥ፣ ሰርቸ የተሻለ ህይወት እኖራለሁ ብሎ ማለም ቅዠት ሆኗል። ከዚህ ይልቅ ያብዛኛውን ወጣት ተስፋ ሀገር ጥሎ በገፍ መሰደድ ከሆነ ውሎ አድሯል።የወያኔ ስርአት የተመቻቸው ለስርአቱ ሹመኞችና ለዘመድ አዝማድ ከዚያ ከተረፈ ለጎሳ ተወላጆቻቸው ብቻ ነው። ሀገሪቱ ውስጥ ተገኘ የሚባል የኢኮኖሚ እድገት ካለም ከዚሁ ከጠባብ ቡድን ጥቅም አልፎ መከረኛውን ህዝብ የሚጠግን አልሆነም።የሀገራችን የህዝባችንና የያንዳንዳችን የተሻለ ህይወትና ዘመን ተስፋ የተቀመጠው ወያኔ መቃብር ላይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

No comments:

Post a Comment