Monday, May 13, 2013

በባህር ዳር ከተማ ከ16 በላይ ሰዎች ተገደሉ

ሰበር ዜና፣ በባህር ዳር ከተማ ከ16 በላይ ሰዎች ተገደሉ

እሁድ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ የአባይን ድልድይ እንዲጠብቅ የተመደበ የፌደራል ፖሊስ አባል እያነጣጠረ ሰዎችን ሲገድል አምሽቷል። የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ16-18 ንጹሀን ዜጎች ያለምንም ምክንያት ከፌደራል ፖሊሱ በተተኮሱ ጥይቶች ተገድለዋል።
የፌደራል ፖሊሱ እያነጣጠረ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል በአቅራቢያው የነበሩ የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበው እንደቆዩ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
የብአዴን ጽ/ቤት ጠባቂዎች በግለሰቡ ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ህይወት ሊታደጉ ሲገባቸው ይልቁኑም ሰውየውን ለመያዝ በመፈለግ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ግለሰቡ ያገኘውን ሰው እየተኮሰ ሲገድል እንደነበር በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል።
ሁኔታው በባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ መረበሽ መፍጠሩ ታውቋል። የከተማው ነዋሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ የተካሄደውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለማውገዝ እንደሚፈልጉም ዜናውን ያቀበሉን የባህር-ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በበኩሉ ዜናውን እንዲህ ዘግቦታል)
 http://www.youtube.com/watch?v=_L1Wnd8Ifcg&feature=player_embedded#!

No comments:

Post a Comment