Thursday, May 30, 2013

የኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል በተከሰሱት በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ለሊሳ፣ ወልቤካ ለሚን ላይ ተፈረደባቸው

Free Bekele Garba and Olbana Lellisa

የመንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት “ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ሽፋን በማድረግ  የአሸባሪቡድን የሆነው ኦነግ አባል ሆነዋል” በሚል በተከሰሱት በአቶ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ውስጥሚገኙ ግለሰቦች ላይ ፍርድ መስጠቱን የዜና ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አመለከቱ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪው አንደኛ ተከሳሽ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ኦልባና ለሊሳ ፣ ወልቤካ ለሚ ፣ አደም ቡሳ ፣ ሀዋ ዋቆ ፣ መሀመድ ሙሉ ፣ ደረጀ ከተማ ፣ አዲሱ ሞክሬና ገልገሎ ጉፋ የቀረበባቸው ክስ “የኦሮሚያ ክልልን ከፌዴሬሽኑ ለመገንጠል ፣ የአሸባሪ ቡድን የሆነው ኦነግ አባል በመሆንና ኬኒያ ድረስ በመሄድ ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ” የሚሉ መሆናቸውን ዘጋቢዎች ጠቁመው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከመስጠቱ አስቀድሞ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ የተለያዩ የፍርድ ማቅለያዎችን ማቅረባቸውን ዘግበዋል። በዚህም መሠረት በመንግስት አቃቤ ሕጎች “የአሸባሪነት ክስ” በቀረበባቸው ላይ አንድም ጊዜ በነጻ ፈትቶ የማያውቀው በሚል የሚተቸው ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የሰጠው ፍርድ የሚከተለው ነው። 1ኛ. አቶ በቀለ ገርባ – በ8 ዓመት እሥር 2ኛ. ኦልባና ለሊሳ – በ13 ዓመት እስር 3ኛ. ወልቤካ ለሚ – በ7 ዓመት እስር 4ኛ. አደም ቡሳ – በ3 ዓመት እስር፣ 5ኛ. ሀዋ ዋቆ – በ8 ዓመት፣ 6ኛ. መሀመድ ሙሉ- በ 10 ዓመት እስር 7ኛ. ደረጀ ከተማ – በ8 ዓመት እስር፣ 8ኛ. አዲሱ ሞክሬ – በ10 ዓመት እስር 9ኛ ገልገሎ ጉፋ – በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ ከሁለት እስከ አራት ዓመት ለሚደርስ ጊዜም ህዝባዊ መብታቸው ፍርድ ቤቱ መሻሩም ታውቋል። በቀለ ገርባ በተለይ ከአቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኋላ የኦፌዴን ፓርቲን ጥሩ ተፎካካሪ ያደርገዋል ተብሎ የሚጠበቅ መምህር ነበር ሲሉ የሚያውቁት ይናገራሉ። መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተደብቆ ተገኘ በተባለው መትረየስ እና ባዶ ሠንሰለት ምክንያት “የተንኮል ድርጊቶችን ግዙፍ በሆነ ዓይነት ማሰናዳት ወንጀል” በሚል ክስ ጭምር የተከሰሱት 9ኛው ተከሳሽ ገልገሎ ጉፋ ከ1984 እስከ 2002 ዓ.ም የኦነግ አመራር አካል የነበሩ ሲሆን በ2002 ዓ.ም ግን ከሌሎች ከኦነግ አባላት ጋር ሆነው እጃቸውን ለመንግሥት ሲሰጡም የኦነግን ዓላማ ኮንነው ሃገር ቤት የገቡ መሆናቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment