Monday, May 13, 2013

ግለሰቦችን በሙስና የማሰር ሂደቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ፤ በተለይ ግልጽ ሌብነት ውስጥ የገቡት እና ንብረታቸውን ለማስመዝገብ አሻፈረኝ ያሉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ ጄነራሎቹ እና ሌሎች የህወሃት ሰዎች አስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አስመላሽ ወልደስላሴም በቁጥጥር ስር ዋለ!


(EMF) የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ የፓርላማ ተመራጭ እና በፓርላማው የህግ እና አስተዳደር ሃላፊ ናቸው። ሁልጊዜ ከቀድሞው ሟች መለስ ዜናዊ ኋላ ነበር ፓርላማ ውስጥ የሚቀመጡት። ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ጀርባ ሰውን ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። ምናልባት ጥቃት እንዳይሰነዘርባቸው በማለት የቅርብ ሰው ካልሆነ በስተቀር የሚቀመጥ ሰው የለም ነበር። አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ግን የህወሃት አባል ከመሆናቸውም በተጨማሪ አይነ ስውር በመሆናቸው፤ በመለስ ዜናዊ ኋላ እንዲቀመጡ ይደረግ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ከላይ የጠቀስነው ዝርዝር አንባቢዎች ግለሰቡን እንዲያስታውሱ ያህል እንጂ፤ ካነሳነው ርዕስ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ላይኖረው ይችላል።
Asmelas Woldeselassei
Asmelas Woldeselassei

ሆኖም ከአገር ቤት ያገኘነው ተጨማሪ ዜና እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል። ትላንት እሁድ ከጠዋት ጀምሮ፤ ቤቱ በፌዴራል ፖሊሶች ተከቦ የነበረ ሲሆን፤ አመሻሽ ላይ በፖሊሶች መወሰዱን ለማወቅ ችለናል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይ የተባለችው የህወሃት አባል እና በቁጥጥር ስር ውላለች። ግለሰቧ የታሰረችው ከጥቂት ቀናት በፊት የታሰረው የባለቤቷን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መረጃዎችን በማሸሽ በመደበቋ መሆኑ ተገልጿል።

ግለሰቦችን በሙስና የማሰር ሂደቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ፤ በተለይ ግልጽ ሌብነት ውስጥ የገቡት እና ንብረታቸውን ለማስመዝገብ አሻፈረኝ ያሉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ ጄነራሎቹ እና ሌሎች የህወሃት ሰዎች አስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment