Saturday, February 15, 2014

በመቱ ዩንቨርስቲ 13 ተማሪዎች ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ተወንጅለው ከትምህርት ገበታቸው ተባረሩ

የበደሌ ቢራ እስፖንሰር መሆንን ተከትሎ ከተፈጠረው ተቋውሞ ጋር በተያያዘ በመቱ ዩንቨርስቲ 13 ተማሪዎች ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ተወንጅለው ከትምህርታቸው ተባረዋል፡፡
የካቲት 4/2014 እ.አ.አ የመቱ ቄሮ በፃፈው ሪፖርት እንደገለፀልን አምባገነኑ የወያኔ መንግስት የመቱ ዩንቨርስቲ ኢንጅነሪግ ተማሪ የሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ያለአንዳች ጥፋት ከትምህርት ገበታቸው አባሯቸዋል፡፡ አምባገነኑ የወያኔ መንግስት ዛሬም እንደልማዱ በመቱ ዩንቨርስቲ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ አመት ያሉ ለአገር ተስፋና መከታ የሚሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ያለጥፋታቸው ከትምህር ገበታቸው በማስተጓጎል 11 የኢንጅነሪግና  ሌሎች ዲፓርትመንት ተማሪዎችን ከትምህርታቸው ከ1-3 አመት ያገደ ሲሆን ጃራ ገሙ የተባለ አንድ ተማሪ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ከትምህርት ገበታው መባረሩንና  ሌሎች 2 ተማሪዎችም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን ያስረዳል፡፡
የወያኔ መንግስት በእነዚህ የኦሮሞ ልጆች ላይ ባወጣው ማስታወቂያም የዩንቨርስቲውን ቅጥር ግቢ ለቀው እንዲወጡ ያሳወቀ ሲሆን እነዚህ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ አመት ያሉ ተማሪዎች ያለጥፋታቸው ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ከትምህርት ገበታቸው ተባረዋል፡፡ የተማሪዎቹ ስም ዝርዝርም እንደሚከተለው ይቀርባል፡-
  1. ጃራ ገሙ – የትውልድ ቦታ ም/ዕ ሸዋ፣ የሁለተኛ አመት የሲቪል ኢንጅነሪግ ተማሪ የሆነና ሙሉ ለሙሉ ከትምህርቱ የተባረረ፤
  2. ደቻሳ ገመዳ – የትውልድ ቦታ ም/ስ ወለጋ፣ የሁለተኛ አመት የሲቪል ኢንጅነሪግ ተማሪ ሲሆን ለ2 አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  3. ቢቂላ ለሚ – የትውልድ ቦታ ም/ስ ወለጋ፣ የአንደኛ አመት የሲቪል ኢንጅነሪግ ተማሪ የሆነና ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  4. ሽፈራው ጉዲሳ – የትውልድ ቦታ ም/ዕ ሸዋ፣ የሁለተኛ አመት የመካኒካል ኢንጅነሪግ ተማሪ ሲሆን ለ1 አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  5. ተካ አሰፋ የትውልድ ቦታ ም/ዕ ሸዋ፣ የሁለተኛ አመት የመካኒካል ኢንጅነሪግ ተማሪ የሆነና ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  6. እያሱ ቃኖ – የትውልድ ቦታ ም/ዕ ወለጋ፣ የሁለተኛ አመት የመካኒካል ኢንጅነሪግ ታማሪ ሲሆን ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  7. ገመቺስ በዳሳ – የትውልድ ቦታ ም/ዕ ወለጋ፣ የሶስተኛ አመት የሒሳብ ተማሪ ሲሆን ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  8. በዳሳ ዱፌራ – የትውልድ ቦታ ም/ስ ወለጋ፣ የሁለተኛ አመት የኤሌትሪካል ኢንጅነሪግ ተማሪ ሲሆን ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
  9. ካሳሁን ማሙዬ – የትውልድ ቦታ ኢሉባቦር ዞን፣ የሶስተኛ አመት የመካኒካል ኢንጅነሪግ ታማሪ ሲሆን ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
10. ጌታ ንጉሴ – የሁለተኛ አመት የኤሌትሪካል ኢንጅነሪግ ተማሪ ሲሆን ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
11. አብዱልከሪም አብዱላሂ የሁለተኛ አመት የኤሌትሪካል ኢንጅነሪግ ተማሪ የሆነና ለአንድ አመት ከትምህርቱ የታገደ፤
12. ነሞምሳ – የትውልድ ቦታ ም/ስ ወለጋ፣ የሁለተኛ አመት የኤሌትሪካል ኢንጅነሪግ ታማሪ ሲሆን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው፤
13. ቢሊሱማ ሙልኢስና – የትውልድ ቦታ ም/ዕ ሸዋ፣ የሁለተኛ አመት የጤና /HO/ ተማሪ ሲሆን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ናቸው፡፡
ከላይ ስማቸው የተጠቀሱ ተማሪዎች ምንም አይነት ጥፋት ሳይፈፅሙ አምባገነኑ የወያኔ መንግስት ሆን ብሎ ስማቸውን በማጥፋት ደም የሚያፈላ ቃላትን በመጠቀም በጥር ወር የኦሮሞ ልጆችን መሳደቡ ይታወሳል፡፡ የሀበሻ ንጉስን የሚያወድስ ዘፋኝ በደሌ ቢራ ስፖንሰር እንዲሆንም አድርጓል፡፡ በዚህ ወቅት የኦሮሞ ተማሪዎች የኦሮሞን ስም የሚያጎድፍ ስድብና የበደሌ ቢራ ስፖንሰር መሆንን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት የዩንቨርስቲውን አስተዳደር ኃላፊ ፍቃድ የተጠየቁ ቢሆንም ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ የወያኔ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው በዩንቨርስቲው ቅጥር ጊቢ በመግባት ተማሪዎቹን መደብደብና ማሰር ጀመሩ፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ 13 የኦሮሞ ተማሪዎች ያላንዳች ጥፋታቸው ከትምህርት ገበታቸው እንዲባረሩ ተደርገዋል፡፡

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!!

No comments:

Post a Comment