Friday, January 16, 2015

አረመኔ የወያኔ መንግስት ጋር የተጋፈጡበት እና ለመብታቸው ሲታገሉ የተሰውትን የኦሮሞ ሕዝብ ምን ግዜም አንረሳቸውም።

By  Afomia yosef
ባሳለፍነው በሚያዝያ እና የግንቦት ወር የኦሮሞ ተማሪዎች የከፈሉት መስዋትነት ከሕፃን እስከ አዋቂ የተካፈሉበት እና አልበገር ባይነታቸዎን ያሳዩበት ከታንክ እና መትረየስ ጋር ከታጠቀ አረመኔ የወያኔ መንግስት ጋር የተጋፈጡበት እና ለመብታቸው ሲታገሉ የተሰውትን የኦሮሞ ሕዝብ ምን ግዜም አንረሳቸውም።  ለመብታቸው ሲሉ ሲታገሉ የተሰውትን ስትዘክር ትኖራለች።ወያኔ ከሌላው ሕዝብ በተለየ የኦሮሞን ሕዝብ ኢላማ ያደረገው ወይም ያነጣጠረው አያሌ ምክንያቶች ውስጥ በተፈጥሮ ሀብቷ፣ በአልበገር ባይነቱ፣ ባህል እና ታሪኩን ጠባቂነቱ የቆዳ እና የሕዝብ ብዛቱ ለአብነት ያህል የሚጠቀሱ ናቸወ።ችግሩ አንዱ አምባገነን ከሌላው አምባገነን  ትምህርት አለመውሰዱ ነው።በዚህም ምክንያት የዲሞክራሲ እና ሰባዊ መብቶች በኃይል እየተነጠቁ በየቀኑ ብዙ ሰው አልቆል አያለቀም ነው ምሁሩን ፣ ወጣቱን፣ ሕፃናትን፣ ሴት እና ወንድ ሳይሉ የንፁሀን ሕይወት አጥፍትተዋል ብቻ በመላዉ ኦሮምያ የተደረገው የኦሮሞ ተማሪዎች የተቀናጀ እንቅስቃሴ የመጭዉ ብሩህ ተስፋ የኦሮምያ አዲሱ ትውልድ አልበገር ባዩ ነው እንደሆነ የሚያረጋግጥልን እውነት ነው።የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች የተጨቆኑ ሕዝቦች ጋር በመሆን ሰባዊ አና ዲሞክራሲያዊ መብቱን ለማስጠበቅ ታግሎዋል እየታገለም ነው ለዚህም ይህ የማይባል መጠነ ሰፊ መሰዋትነት ከፍሎል እየከፈለም ይገኛል።
ድል ለሰፊው ኦሮሞ ሕዝብ!!

No comments:

Post a Comment